ኢሳት (ግንቦት 9 ፥
2008)
በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው እየተወሰዱ እንደሆነ ታወቀ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎችም ሰሞኑን የተመታውን የምግብ ማቆም አድማ ተከትሎ 5 የሚሆኑ ስማቸው ያልተገለጹ ተማሪዎችን ከግቢ አፍነው በመውሰድ የት እንዳደረሷቸው እንዳልታወቀ ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች ከሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተናግረዋል።
እነዚህ ተማሪዎች ታፍነው የተወሰዱበት ምክንያት ፖለቲካዊ ሊሆን እንደሚችልና ከዚህ በፊት በተደረጉ ተቃውሞ እንቃስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል ተብለው ተጠርጥረው ሊሆን እንደሚልች ኢሳት ያነጋገራቸው እነዚህ የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ከህዳር ወር ጀምሮ የቀጠለው ተቃውሞ ለጊዜው ጋብ ያለ ቢመስልም፣ በአሁኑ ወቅት በግቢው ውስጥ እጅግ ብዙ የመከላከያ ሰራዊት ተሰማርቶ እንደሚገኝ ታውቋል።
አሁን የሴሜስተሩ ፈተና እየተቃረበ በመጣበት ጊዜ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንዳንድ ተማሪዎች እያፈኑ መውሰዳቸው ተማሪዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው የኢሳት ምንጮች ከስፍራው አስታውቀዋል።
No comments:
Post a Comment