የሺዋስ አሰፋ እና ዳንኤል ሾበሺ ከእሥር ተፈቱ። የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባልና የብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሲሆን፣ ዳንኤል ሺበሺ ደግሞ በምርጫ ቦርድ በጉልበት ሕጋዊነቱን የተነጠቀው የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/ል
የደርጅት ጉዳይ ሃላፊ ነበር።
ሐመሌ 1 አንድ
2006 ዓ.ን በሽብርተኝነት ክስ የተከሰሱት ዳንኤል እና የሺዋስ ከንድ አመት ከሁለት ወር በኋል ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም
የመጀመሪያ ችሎት ፍርድ ቤት መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ቢለቃቸውም፣ አቃቢ ሕግ ይግባኝ በመየጠቁ ሳይፈቱ ቀርተው ነበር። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ከሰባት ወራት በኋላ ዉጭ ሆነው እንዲከራከሩ ቢወስንም፣ ፍርድ ቤትን በመዳፈር በሚል የአንድ አመትብቅጣት ተበይኖባቸው ስለነበረ፣ማረሚያ ቤቱ አለቀቀም በማለቱ እስከ ዛሬ ድረስ በግፋ በጭካኔ በወህኒ ተሰቃይተዋል።
ሰው የገደለ ወደ ሰባት አመት ተፈርዶበት፣ በተመክሮ በሶስት አመት ዉስጥ እንዲወጣ እየተደረገ፣ ፍርድ ቤትን ተዳፈራችሁ ተብሎ ሁለት አመት በወህኒ እንዲቆዩ ማድረግ ምንም ያህል በአገራችን ኢትዮጵያ የፍትህ ስርአቱ የተጨማለቀ መሆኑን አመላካች ነው።
የሺዋስ እና ዳንኤል መታሰር አለነበረባቸውም። ለሁለት አመት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው የታሰሩት አገራቸውን እና ሕዝብናቸው ስለወደዱ ነው። አገርን መዉደድ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው ወንጀልና ሽብርተኝነት የሆነው።
የሺዋስን እና ዳን፤ኤልን እንኳን ለቤታቸው አበቃችሁ እያልን፤ ሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ አሁን በወህኒ በስቃይ ላይ እንዳሉ እያሰብን፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትግሉን ማይጠናከር ይጠበቅብናል።
ሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ አሁን
No comments:
Post a Comment