Thursday, May 26, 2016

በቂሊንጥ ወህኒ ቤት ታስረው የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪዎችና ሌሎች ተከሳሾች ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታ አቀረቡ

በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንቶ ወህኒ ቤት የሚገኙ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪዎችና ሌሎች ተከሳሾች ክሳቸው በመቋረጡ አቤቱታ አቀረቡ።
ለሃገራችንንና ለህዝባችን የሚበጀውን በማሳሰባችን በአሸባሪነት መከሰሳችን ሳያንስ የፍርድ ሂደቱ ተቋርጦ በወህኔ ቤት ውስጥ ያለ አንዳች ምክንያት መቀጠላችን አግባብ አይደለምሲሉም ለፍትህ ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ አመልክተዋል።
የበረራ ባለሙያዎች እነ የመቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና አበባ ተመስገን በሚሉ የክስ ፋይሉች በአሸባሪነት ተከሰው በቂሊንጦ ወህኔ ቤት የሚገኙት 32 ተከሳሾች ለፍትህ ሚኒስትር በጻፉትና ለኢሳት ዘግይቶ በደረሰው ደብዳቤያቸውበሽብር በተጠረጠርነው አካላት ላይ ያለው የፍትህ አሰጣት ሂደት ከሚገባው በላይ እየዘገየ በእኛ በተከሳሾችና ቤተሰቦቻችን ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ስነልቡናዊ ጫና እያስከተለ ይገኛል፣ ባልታወቀ ምክንያትም ቀጠሯችንና የክሱ ሂደት ተቋርጧልሲሉ ዘርዝረዋል።
በዚሁ በቂሊንጦ ወህኒ ቤት 10 መዝገቦች 200 በላይ ከአማራ ክልል የመጡ ወጣቶችና አዛውንቶች እየተጉላሉ መሆናቸውን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢ የመጡትና በተመሳሳይ ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ተከሳሾቹ ከፍትህ ሚኒስቴር ባቅረቡት አቤቱታ ላይ አስፍረዋል።
በሃገራችን በሁሉም መስክ ያለው ችግር ለመፍታት በሰላማዊ መንገድ መታገል ህገ-መንግስታዊ መብታችን ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ግዴታችን ጭምር ቢሆንም 2007 ምርጫ ማግስት ከየቤታችን እየተለቀምን ታሰርን፣ የሃሰት ክስም ተቀነባበረብን ሲሉ ዘርዝረዋል። ኢህአዴግ ዕድሎችን እያበላሸ፣ ታጥቦ ጭቃ እየሆነ የኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት አደረጋት በማለትም ከታሰሩበት ጥቅምት ወር 2007 ጀምሮ የደረሰባቸውንም በደል ዘርዝረዋል።
በመጨረሻም ጉዳያቸው በቋሚና መደበኛ ችሎት እንዲታይ የጠየቁ ሲሆን፣ በተዘዋዋሪ ችሎት የሚቀጥል ከሆነ በክልላችን በአማራ እንዳኝ ሲሉ ጠይቀዋል። ክሱ ተቋርጦም ከሆነ /ቤቱ በነጻ ያሰናብተን በማለት የጠየቁት 32 እስረኞች፣ በወህኒ ቤት ውስጥ ያሉበት ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ጠቅሰው፣ ለሚደርስባቸው ጉዳት ሃላፊነቱ የመንግስት ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ኢሳት








No comments: