Friday, May 13, 2016

“ሽብርተኛ” ከተባሉ 85% ነጻ መባል የጸረ–ሽብር ሕጉ ችግር እንዳለበት አመላካች ነው – ግርማ ካሳ

ዘላለም ወርቃገኘሁ 5 አመት ከ4 ወር፣ ተስፋዬ ተፈሪ 3 አመት ከ11 ወር፣ ሰለሞን ግርማ ደግሞ 3 አመት ከ3 ወር የእሥር ቅጣት ተወስኖባቸዋል። ቅጣቱ እስረኞቹ ከታሰሩበት ጊዜ ጀመሮ እንደሚሆን ፍርድ ቤቱ ገልጿል። ያ ማለት ዘላለም ወርቃገኘው ከዚህ በኋላ 4 አመት፣ ሰለሞን ግርማ አንድ አመት ከ7 ወር ፣ ተስፋዬ ተፈሪ ደግሞ 2 አመት ከ5 ወር ፣ ተመክሮ ካልተሰጣቸው፤ ይግባኝ ብለው ዉሳኔው እንዲቀለበስ ካላተደረገ ወይንም የመንግስት ለዉጥ ካልመጣ ፣ በእሥር ይቆያሉ ማለት ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ ሶስት ወራት ቀደም ብሎ፣ ሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም ዞን ዘጠኞችም የሽብርተኝነት ክስ መከሰሳቸው ይታወቃል። እነርሱም አስር ነበሩ። አምስቱን፣ ዘላለም ክብረትን፣ ኤዶም ካሳዬን፣ ማህሌት ፋንታሁንን፣ ተስፋሁን እና አስማማዉ፣ ራሱ አቃቢ ሕግ “ክሳቸዉን አንስቻለሁ” ብሎ እንዲፈቱ አደረገ። አራቱን፣ ናትናኤል ፈለቀን፣ አቤል ዋቤላን፣ ሶሊያና ሺመልስንና አጥናፍ ብርሃኔን፣ መከላከል አያስፍልጋቸው ብሎ ፍርድ ቤቱ ነፃ አላቸው። በፍቃዱ ሃይሉን ተከላከል ተባለ።
አቃቢ ሕግ በነዘላለም ወርቃገኘው መዝገብ ለተከሰሱ ተከሳሾች ያቀረበው መረጃ ተመሳሳይ ነው። ለዞን ዘጠኞች ያቀረበውም መረጃ ተመሳሳይ ነው። በነዘልልም ወርቃገኝው መዝገበ ክተከሰሱት ሶስቱን ፣ ዘላላለም ወርቃገኘው፣ ሰለሞን ግርማና ተስፋዬ ተፈሪ ላይ ብቻ የጥፋተኝነት ዉሳኔ ማሳለፉ፣ ከዞን ዘጠኞች ደግሞ በበፍቃዱ ሃይሉ ተለይቶ ተከላከል መባሉ አስገራሚ ነው።
እንግዲህ ሁለት ትላልቅ ነጥቦችን ማየት እንችላለን። ተከሳሾች ተመሳሳይ ክስ ቀርቦብቸው፣ ተመሳሳይ መረጃ ቀርቦ፣ አንዱ ተፈቶ ሌላው መታሰሩ፣ የፍትህ ሂደቱ ፍትህ የሚንጸባረቅበት ሳይሆን ፣ ጨዋታና ቀልድ እንደሆነ የሚያመላክት ነው። ይመስለኛል ሁሉን ከፈታን ለምን መጀመርያ አሰራችሁ እንባላለን በሚል ይመስለኛል ተመሳሳይ ክስ ቀርቦ፣ ተመሳሳይ መረጃ ቀርቦ የተወሰኑት ብቻ እንዲቀጡ የተደረገው። በርግጥ ጥፋት ተሰርቶ ሳይሆን “ምን እንባልላለን” ከሚል የተነሳ ።
ሁለተኛ እነ ዘላለም ወርቃገኘሁን እና ዞን ዘጠኞችን ደምረን በሽብርተኝነት ክስ ከተከሰሱ ሃያ እስረኞች መካከል ፣ ወደ ሁለት አመት የፍርድ ቤት መንገላትት በኋላ፣ ጥፋተኛ የተባሉት 3 ብቻ ናቸው። 85% የሚሆኑት በነርሱ ላይ የቀረበዉን የሽብርተኝንት ክስ ፍርድ ቤት ዉድቅ ነው ያደረገው። ይሄ የሚያሳየው ምን ያህል የሕወሃት ደህንነት መስሪያ ቤት፣ የጸረ-ሽብርተኝነት የሚባለውን ጸረ-ህዝብ የሆነ ሕግ እየተጠቀመ፣ ዜጎችን እያሸበረበት እንዳለ ነው። 85% ተከሳሾችን ፍርድ ቤቱ ነጻ ካደረጋቸው፣ የሕጉ አጠቃቀም ላይ፣ ወይም ሕጉ ላይ ትልቅ ችግር አለ ማለት ነው።
ይህ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ ሽብርተኝነትን እየተከላከለ ሳይሆን፣ ተጠያቂ ያልሆኑና ከልካልይ የሌላው እነ አቶ ጌታቸው አሰፋና የደህንነት ሃላፊዎች፣ ሕዝቡን እንዲያሸብሩ መሳሪያ እየሆናቸው ነው። ይህ ሕግ መሰረዝ ወይንም እንደ አልሻባብ፣ አይሰስ ባሉ ሽብርተኞች ላይ ብቻ እንዲያነጣጠር ተደረጎ መሻሻል አለበት። “ሽብርተኛ” ተብለው የተከሰሱ ሁሉ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው። ኢትዮጵያ ዉስጥ በሕዝብ ላይ ጉዳት ያደረሰ፣ የታሰረ፣ ቦም ወይይንም ፈንጂ ይዞ የተገኘ “ሽብርተኛ” የለም። ሽብርተኞች ተብለው እየታሰሩ ያሉት ጦማሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ናቸው። አገርን እና ህዝብ መዉደድ፣ ለአገርና ለሕዝብ መቆም፣ ሕግ መንግስቱ ላይ የተደነገገዉን የመጻፍና የመናገር መብት መጠቀም “ሽብርተኝነት” እያስባለ ያለው። አንድ ባለስልጥጣን አይቷችሁ ካልወደዳችሁ በቀጭን ት እዛዝ መመሪይአ አስተላልፎ ሽብርተኛ ተብላችሁ ወደ ወህኒ ልትወረወሩ ትችላላችሁ። ማንም ዜጋ ሽብርተኛ ከመባል የሚያድነው ንገር የለም። ያን ያህን በአገራችን በሽብር ስም ትልቅ መንግስታዊ ሽብር እየተፋፋመ ነው።
(በነገራችን ላይ ሽብርተኞች ስለሚሆናቸው አቃቢ ሕግ ካቀረባቸው መረጃዎች የተወሰኑቱ ክግንቦት ሰባቱ ና የጥፋት ኃይሉ ግርማ ካሳ ተነጋግራቹሃል የሚል አላበት። አያስቁም ….ግርማ ካሳን የግንቦት ሰባት አባልና የጥፋት ኃይል አድርገው ሲወስዱ። ያን ያህል ሰዎቹ ሰዉን ዝም ብለው፣ ነገሮችን ሳይመረምሩ እያግበሰበሱ እንደሚከሱ ይሄ ራሱ አንድ ማሳያ ነው። )

No comments: