Thursday, May 26, 2016

የኢህአዴግ አባላት ከክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ እየጎረፉ ነው

ግንቦት ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የወጣበት የኢህአዴግ በአል አከባበርን በተመለከተ ውስጥ ሆኖ ዝግጀቱን በመከታተል ላይ የሚገኘው ዘጋቢያችን ትዝብቱን ልኳል።
ትላንት ብዙ በአ. ከተማ የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩና የፌደራል ሚኒስቴር /ቤቶች በተሰጣቸው ትዕዛዝና በወጣላቸው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት የኮንትራት ትራንስፖርት እየተጠቀሙ የመንግስት ሥራ ዘግተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የክ/ከተማና ወረዳ /ቤቶች እንዲሁም በህዝብ ፖለቲካ አደረጃጀት ውስጥ የታቀፉ ደግሞ በየአካባቢያቸው በሚገኙ መሰብሰቢያ አዳራሾች ውስጥ ከላይ በወረደው ወጥ የሆነ የኢህአዴግ የምዕተ ዓመት የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚያትት ሰነድ ላይ ውይይት አድርገዋል። ከውይይቱ በሁዋላ ወደ ተዘጋጀላቸው መስተንግዶ ያመሩ ሲሆን፣ በቆይታቸው መጠንም በቀን 150 ብር የውሎ አበል ይከፈላቸዋል፡፡

በቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ላይ ስለታዘበው ነገር ሲገልጽ ደግሞሁሉም የህዝብ የፖለቲካ አደረጃጀቶች በተለይ ስራአጥ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አዛውንት እናትና አባቶች ሃይገር ባስ የተመደበላቸው ሲሆን፤ ተሽከርካሪዎቹ የአዳራሹን አጥር ዙሪያና የአካባቢው የመኪና መቆሚያ ቦታ አጣበው ቆመዋል። በተጨማሪም የከተማዋ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ተማሪዎች በተመሣሣይ ሁኔታ ትምህርታቸውን ዘግተው እንዲገኙ በመታዘዛቸው ከነዩኒፎርማቸው ተገኝተው ነበር። ይሄው የዝግጅት ፕሮግራም እስከ ግንቦት 20 ድረስ በተያዘለት መርሃ ግብር መሠረት የሚቀጥል ይሆናልብሎአል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ እንግዶች በተለያዩ የከተማዋ ሆቴሎች አልጋ ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ለግንቦት 20 የተዘጋጀውን ቀይ ኮፍያ አድርገው መታየታቸውን የገለጸው ወኪላችን፣ የሃገሪቱ ወጣት ሊግ አባላት በዝግጅቱ ለመገኘት ረቡዕ ዕለት ማታ . ገብተዋል ብሎአል።
የህዝቡን አስተያየት በተመለከተ ሲገልጽ ደግሞህዝቡን በችግርና በሙስና እያንጫጩ በዓል እናከብራለን ማለት ምንድነው? 50 ዓመት በዓል ያድርሰን እያሉን ነወይ? “ ሲሉ እንደሚጠይቁ ገልጾ፣ በመንገድ ላይ ደንኳኖችን ተክለው ህዝቡ እንዲጎበኝ ለማድረግ ጥረት ቢያደርጉም የሚጎበኝ በመጥፋቱ ድንኳኖቻቸውን ማንሳት ጀምረዋልሲል ትዝብቱን አጠናቋል።

No comments: