ሚያዚያ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት ስር በመትተዳደረዋ ትግራይ የሚኖሩ አርሶደአሮች በረሃቡ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች እየተሰደዱ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አርሰዶአደሮች ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት የሚጠይቁ ከትግራይ የመጡ አርሶዶአሮች በብዛት እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን፣ አርሰዶአደሮቹ በድርቁ ምክንያት መሰደዳቸውን እንደነገሩት ገልጿል።
ወደ አዲስ አበባ ከመጡ አንድ ወር ያክል የሆናቸው አርሶአደር፣ በድርቁ ምክንያት የሚቀመስ በመጥፋቱ መሰደዳቸውን ይናገራሉ።
በአካባቢያችን ያለው ድርቅ እንድንሰደድ አደረገን የሚሉትን አርሶአደር፣ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ ሳምንት እንደሞላቸው ተናግረዋል። ሌለው ቄስ አርሶአደርም እንዲሁ እርሳቸውና በአካባቢያቸው የሚኖሩ ሰዎች ረሃቡን በመሸሽ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ገልጸዋል ።
ልጆቿን ይዛ ለመሰደድ መገደዷን የገለጸችው እናትም፣ በአካባቢው የገባው ረሃብ እንድትሰደድ እንዳደረጋት ገልጿል ። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ደብር ተክለሃይማኖት ቀበሌ በወረዳው በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የተላከ 100 ኩንታል እህል መጥፋቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ፖሊሲና ሚሊሺያ በእየቤቱ ሲፈትሹ በየቀበሌ አመራሮች ቤት መገኘቱን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ዘራፊዎቹ ምንም እርምጃ ሳይወሰድባቸው መቆረቱን ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment