Tuesday, May 10, 2016

ደቡብ ሱዳን ‹‹ህጻናቱን ገና አላስረከብኩም›› እያለች ‹‹19ኙ ተመለሱ››የሚባለው ከየት ነው ?

gambila
gambila
ደቡብ ሱዳን ‹‹42 ህጻናትን አግኝቻለሁ፣የሚመለሱበትን ሁኔታም እየተነጋገርኩ ነው››አለች
(ሳተናው)  የደቡብ ሱዳን ፑማ ክልል ገዢ ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን እንደሚያስመልሱ አስታውቀዋል፡፡በሚያዚያ ወር የሙርሌ ጎሳዎች አባላት እንደሆኑ የተነገረላቸው ታጣቂዎች ከ200 የሚልቁ ኢትዮጵያዊያንን በመግደል እንስሳቶችን ዘርፈው ከ125 ልጆችን አፍነው መውሰዳቸው አይዘነጋም፡፡
የፑማ ክልል ኃላፊዎች ታፍነው የተወሰዱትን ልጆች ወደቤተሰቦቻቸው ለመመለስ የቻሉትን ያህል እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡
የቡባ ክልል መንግስት የኢንፎርሜሽን ሚንስትር ጁሊያ ጄምስ ለራዲዩ ብሊንድኒግ በሰጡት አስተያየት የክልሉ ኃላፊዎች ከማህበረሰብ መሪዎች ጋር በመተባበር ህጻናቱን ለማግኘትና ለማስለቀቅ ያለእረፍት በመስራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ሚንስትሩ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ 42 ልጆች መገኘታቸውን በመጠቆም ቀሪዎቹን ለማግኘትና ከቤተሰቦቻቸው ለማገናኘት ፍለጋው ቀጥሏል ብለዋል፡፡
ሚንስትሩ ለራዲዮው ጨምረው እንደገለጹት ከሆነም የፑማ ክልልና የአገሪቱ መከላከያ ሚንስትር ምክትል ሚንስትር የሆኑት ዳቪድ ያዩ ያዩ ሁኔታውን ለማረጋጋት ወደ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል አምርተዋል ብለዋል፡፡ህጻናቱ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ለማመቻቸትም ከኢትዮጵያ ሰዎች ጋር እየተነጋገርን እንገኛለን ማለታቸው ተወስቷል፡፡
በአንጻሩ የኢትዮጵያ መንግስት የመገናኛ ብዙሃናት 19ኝ ልጆችን ታፍነው ከተወሰዱበት መመለሳቸውንና ከቤተሰቦቻው ጋር መገናኘታቸውን በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡የኢትዮጵያ ወታደሮች የደቡብ ሱዳንን ድንበር አልፈው ባልገቡበት ሁኔታም ልጆቹን አግኝተን አመጣናቸው መባሉ እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ምንጭ ራዲዮ ብሊንዲንግ
Satenaw

No comments: