Monday, May 16, 2016

በርካታ ወታደሮች የኢህአዴግን መንግስትን በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ መቀላቀላቸውን የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ይፋ አደረገ።

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ / ኢሳት ዜና :- ትህዴን ባወጣው መግለጫ ከድተው ወደ ድርጅቱ ከተቀላቀሉት መካከል 14ቱን የትውልድ ቦታ፣ ስም፣ የነበሩበትን ክፍለ ጦር፣ ሬጅመንትና ሻምበል በዝርዝር አመልክቷል።
ከከዱት መካከል አንዳንዶቹ ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ፤ ዕረግ የሌላቸው በርካታ ወታደሮችም ይገኙበታል።
ሥርዓቱን ከድተው ወደ ህዴን መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ወታደሮች በሰጡት አስተያዬት፦እኛ ወታደሮች የገዢው ሰርአት እድሜ ማራዘሚያ ከምንሆን፤ በዚህ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለው የእርስ በርስ ግጭትና ቀወሰ ወደ ከፋ አደጋ ሳይወጣ ጠመንጃ ታጥቀን አገርንና ህዝብን ለማዳን የድርሻችንን ለመወጣት ተሰልፈናልብለዋል።
ወታደር አደም ሙሃመድና ወታደር በሸር የሴፍ በሰጡት አስተያዬት ደግሞ በአሁን ወቅት በአገሪቱ ወታደር ሆነህ ለመኖር አሰቸጋሪ ነው፤ ሰላም ለማስከበር በሚደረገው ተልዕኮ፣ በሚሰጠው ማእርግና በሌሎችም መሰል አሰራሮች አድሎ በመንገሱ በሰራዊቱ መካከል ግልፅ የሆነ ሰፊ ልዩነት መኖሩን አመልክተዋል።
በመሆኑም በሰራዊቱ ውስጥ እምነትና ወኔ አድሮበት ሊቆይ የሚፈልግ የለም አስተያዬት ሰጭዎቹ፤ ያለው ሰራዊት በወሬ እንደሚባለው አንድነቱ የተጠበቀ ሳይሆን እርስ በርሱ የተበታተነ ነው ብለዋል።
በተለይ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ውስጥ በየቦታው በሚነሱት ተቃውሞዎችና ግጭቶች ሳቢያ ቅሬታና ተቃውሞ እየተፈጠረባቸው ያሉ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ሥራቸውን ጥለው እየጠፉ እንደሆነ ከወታደሮቹ አስተያዬት ለመረዳት ተችሏል።

No comments: