ካለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ወዲህ ወያኔ መራሹ መንግስት አንድ ወጥ አመራር የሚሰጥ መሪ በማጣቱ ድግሱ ሁሉ የጨበሬ ተስካር እየሆነ እያስተዋልን ነው። ለዚህም ይመስላል እንደ መና ከሰማይ የወረደላቸውን “ፖለቲካዊ ትርፍ” የሚያስገኝ አጋጣሚ እንኳ በአግባቡ ሊጠቀሙበት ሲሞክሩም አይታዩም። ሰውየው (መ.ዜ) “ልማታዊ” ና “ሽብርተኛ” በሚሉት ቃሎች ላይ ፖዝ አድርጓቸው ሄዶ፦ ፖለቲካውንም፤ ብሄራዊ ሃዘኑንም፤ ሃይማኖቱም፤ ማህበራዊ ቀውሱንም ….. በልማታዊና በሽብርተኛ መነጽር ከማየት፤ በልማታዊና በሽብርተኛ ሚዛን ከመስፈር፤ በልማታዊና በሽብርተኛ ቋንቋ ከመተርጎም በተለየ የሚያውቁት ነገር ያለ አይመስልም።
Source:: Ecadforum
No comments:
Post a Comment