Saturday, May 2, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል በኮሎራዶ በመገኘት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ እና የመን በወገናቸው የደረሰውን ኢ-ሰበኣዊ ድርጊት ኣውግዘዋል::

የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል በኮሎራዶ በመገኘት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ እና የመን በወገናቸው የደረሰውን ኢ-ሰበኣዊ ድርጊት ኣውግዘዋል::

colorado
በኮሎራዶ ግዛት ኢትዮጵያኖች በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ እና የመን በወገኖቻቸው ላይ የደረሰውን ጭቃኔ በመቃወም የ3 ቀን የጸሎት ስነስርአት ባለፈው ቅዳሜ እለት በቅድስት ማሪያም ቤ/ያን ጀምረዋል። 


በዚሁ ጸሎተ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን የአሜሪካን ሀገር የአውሮራ ኮንግረስ ማይክ ኮፍማን፣ የከተማዋ የፖሊሲ ክፍል አዛዥ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር በእለቱ ተገኝተው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
20150425_191151
የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢ/ር ይልቃል በኮሎራዶ በመገኘት በወገናቸው የደረሰውን ኢ-ሰበኣዊ ድርጊት ኣውግዘዋል::
blue party
 የአለም ጠላት የሆነው በኢትዮጵያኖች ያደረገው ጭቃኔ ዝም የሚባል ኣይደለም :: ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና ምቹ የስራ እድል የዲሞክራሲ እጦት መኖሩ እስከቀጠለ ድረስ ኣሁንም ስደቱን ኣያቆመውም ብለዋል::  ኢ/ር ይልቃል ከአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ነበር ሀዘናቸውን የገለጹት::
20150425_201222
ኢትዮጵያኖቹ በኮሎራዶ በሀዘን ተውጠው የተሰዉ ክርስቲያኖችን በማሰብ የዋሉ ሲሆን በርካታ የተለያዩ አገራት ተወካይ እንግዶች በእለቱ ተግኝተዋል::
በኮሎራዶ የግሸን ማሪያም ቤተክርስቲያን ለረጅም ጊዜ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚሰደዱበትና በሚገደሉበት ጊዜ ሁሉ ግንባር ቀደም በመሆን ስደተኞች ምእመናን በማህበራዊና የኢኮኖሚ ድጋፍ በማድረግና በማገልገል የምትታወቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን ለማውቅ ተችሎል::
20150427_171656
በተያያዘ ዜና ሰኞ እለት በኮሎራዶ ምቤት ግቢ ውስጥ ቁጥራቸው በበርካታ ነዋሪዎች በተገኙበት ታላቅ ሰልፍ ተደርጎል:: የከተማዋ ከንቲባ ተወካይ ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ኣብረን እንደምንሰራ ቃል እገባለሁ በለዋል::
20150427_173512
 የአሜሪካ ምቤት ተወካይ ማይክ ኮፍማን አይሽን እንደሚዋጉት እና በኦባማ መንግስት ላይ ግፊት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል:: ይህ ፕሮግራም የተዘጋጀው በሶስት ኮሚውኒቲዎች እንደሆነ ለማወቅ ተችሎል



No comments: