” ….. የለቅሶና የብዙ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ ልጆችዋ ስለሞቱባት መጽናናት እምቢአለች።….” /ማቴዎስ 2፡18/
ኮንፊሽየስ ወደ ጫካ በመሄድ ግዜውን ማሳለፍ ይወድ ነበር ይባላል። ከዕለታት እንድ ቀን እንደተለመደው ወደ አንድ፤ከአካባቢው ‘ርቆ ወደሚገኝ ጫካ አመራ። ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ጥቅጥቅ ባል ጫካ ውስጥ እንደደረሰ ለማርፍ ሲሞክር የገጠመው፤የተለመደው የወፎች ዝማሬና የአበባወችና የዛፎች ውብ ማዕዛ ሳይሆን እጅግ አሳዛኝ ፣ የለቅሶና የሲቃ ድምጽ ነበር። ኮንፊሽየስየሰማውን ማመን እያቃተው ወደዚያው አመራ፤ ወደ ድምጹ እየተጠጋ ሲሄድ፤ አንዲት ሴት ሳሩን እየነጨች መሬቱን እየቧጨረችየ ”ኤሎሄ” ዋይታ ታስተጋባለች። ራሱን ለመቆጣጠር እየሞከረ ቀስ እያለ ተጠጋት። ሊያጽናናትም ሞከረ። ግን የምትጽናና ሴትሁና አላገኛትም። ይሁን እንጂ በዚህ ጫካ ውሰጥ ለምን እንደመጣችና የዋይተዋን ምክንያት እ‘ድትነግረው አግባባት። እሷም ከአንድ ልጇ ጋር ወደዚህ ጫካ ለመኖር እንደመጣችና ልጇ ግን በአውሬዎች እንደተበላባት ቋንቋ ሊገልጸው በማይችል ሀዘን ነገረችው። ‘’አውሬዎች አንድ ልጀን ብሉት።”
ኮንፊሽየስም በመገረም ”ለምን ከተማ ውስጥ አትኖሩም ነበር? እንዴት ጫክ ወስጥ መኖር ትመርጣላችሁ?” በማለት ጠየቀ። ያገኘው መልስ ግን” ጌታዬ ከተማ ያሉት አውሬዎች ከዚህ ጫካ ውስጥ ካሉት አውሬዎች ይብሳሉ፤ የከተማዎቹ አውሬዎች ባሌንና ታላቁን ልጅን በልተዋል፤ የቀረኝንአንድ ልጀን ለማትረፍ ነበር ወደዚህ ጫካ የመጣውት፤ ይኽው እሱንም አጣውት።” አለችው። እኛም ከወያኔ አውሬዎች የተርፉትን ወገኖቻችንበጫካ አውሬዎች አስበላናቸው፣ አሰየፍናቸው::
ግን እኛ ”ያልሞትነው” በህይወት ያለነው ምን እያደረግን ነው? አሁንም እንዳለፈ ሁሉ “መግለጫ እናወጣለን!….. ሻማ እናበራለን!……. ሰላማዊ ሰልፍ እንወጣና፣ ድርጊቱን እናወግዛለን!……. ወያኔ ወገኖቻችን ይታደግ እንላለን (ሃያ አራት ዓመት ሙሉ) ……ወያኔ ደግሞ ቆመጡን ያቀምሰናል፤ ጥይቱን ያጠጣናል፤ እስርቤት ያጉረናል፤ በባዕድ ሀገር እየሄድን እንድንታረድ፣ ከሳአውዲ እስከ የመን፣ ከደቡብ እፍሪካ እስከ ሊቢያ፣ ከሳህራ እስከ ካለሀሪ በርሃ ፣ ከኤደን እስከ ሜድትራኒያን ባህር ብሎም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ዜጋ እስከ አለበት ድረስ ባህር፣ እሳት፣ በርሃና ሰይፍ እንዲበላን ያመቻቸናል።
የገዛ ሀገራችን ለወያኔ አውሬዎች አስረክበናልና፤ መንግስትና ሀገር እስከሌለን ድረስ በየትም ቦታ ብንሄድ የሚጠብቀን በባዕዳን አውሬዎች እጅ መውደቅና መታረድ ነው። ኮንፊሽየስ ጫካ ውስጥ እንዳገኛት እናት።
ከዚህ ላይ ከዚህ በፊት የጦመርኩትን በከፊል በድጋሜ ልጠቀም፤
”ዓለም የም‘ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።” /አልበርትአነስታየን/
እናም የምድርን የሰቆቃና የሞትን አይነት ሁሉ እያስከፈሉን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን እያጠፉ ያሉት፣ እስላማዊ መንግስት ነኝ ባይ (አይሲኤል) ፣ ወያኔ፣ ሳአውዲ አረቢያ/ አረቦች፣ ምእራቡ ዓለም፣ ደቡብ አፍሪካ ወይም ሌላ ሳይሆን፣ እኛ እራሳችን ቁጭ ብለን የምንመለከተው ወይም ለታይታ የምንታይው፣ ኢትዮጵያዊያኖች ነን። እኛ ነን….. በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ተቀምጠን፤ ለወገኖቻችን መሆን ያልቻልነው። እኛ ነን….. ለጠባብ መንደርተኞች ሀገራችን አሳልፈን የሰጠን። ትላ’ትናም ይሁን ዛሬ እውነቱ ይኸው ነው። ይኸን እውነታ ተቀብለን፣ በተለይም በዚች ወቅት ለኅልውናችን ስንል የሚጠይቀውን መሰዋእትነት እስከ አልከፈልን ድረስ፣ ስቃይና ሰቆቃ፤ እንደ በግ መታረድ፣ እንደትላ’ቱና እንደዛሬው ሁሉ፣ ነገም ተባብሶ ይደገማል።
ባለፉት ዓመታት ከሀገርቤት ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እንደ ቅጠል የረገፉትንና የምድራችንን ስቃይ የከፈሉትን ለግዜውም ቢሆን ወደ ጎን ትተን፤ እስቲ ለደቂቃ የአይሲኤል ሰይፍ የበላቸውን ወግኖቻችን የመጨረሻ ሰዓት እናስበው? ሀዘን፣ …ለቅሶ፣ …. ምን ይበቃል? ዋይታችንን የሚገልጽ ቋንቋ በዚች ምድር ላይ ይኖር ይሆን? ኅሊናችን ምን ይለናል? ” ከሞቱት ላልሞትነው” ለኛ ለቀሪዎቹ ሸክሙ አይከብድም? ”ሰው ከንቱ ነውና……” እንደ ትላንትናዎቹ ወግኖቻችን ነገም እነዚህን እንረሳቸው ይሆን? በየትም ቦታና በማንኛውም ግዜና ሁኔታ ብንሆን ፣ በህይወት ላለን ዜጎች የማናመልጠው ነገር ፤ እነሱ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀናጅተው፤ የቤት ስራውን ለኛ ጥለውልን ሄደውል።
ሚያዚያ 2007
ኢ-ሜል: philiposmw@gmail.com
goolgule
No comments:
Post a Comment