የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተጠረጠሩ ኃላፊዎችንና ባለሀብቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ቀጥሏል
የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ በሙስና የጠረጠራቸውን የክልሉ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ኃላፊዎችንና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ባለሀብቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ሲቀጥል፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየተዘጋጀ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡
የክልሉ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ጥንቃቄ የተሞላበት ምርመራ ማካሄዱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ወደ ውጭ አገር ይኮበልላሉ ተብለው የተጠረጠሩ ከአገር እንዳይወጡ መመርያ መተላለፉ ታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከአንድ ሳምንት በፊት በሙስና የጠረጠራቸውን የክልሉ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አሥር ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
እነዚህ ኃላፊዎች በሙስና የተጠረጠሩት ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ጨምሮ በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ሒደት 25 የሥራ ኃላፊዎች ተጠርጣሪ ሆነዋል፡፡
በሙስና ከተጠረጠሩት መካከል የውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢፋ በዳዳና ምክትላቸው አቶ ጎዳና ዳባ ይገኙበታል፡፡
የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር ያልዋሉትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንቅስቃሴ ከማድረጉ ጐን ለጐን፣ በክፍል ሁለት ዘመቻው ከማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል
እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮማሽን ኮሚሽነር አቶ ታከለ እንኮሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የክልሉ ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሚያካሂዳቸው ሥራዎች የኮንስትራክሽን ማሽኖችን የሚያገኘው በሁለት መንገድ ነው፡፡ የመጀመሪያው በግዥ ሲሆን ሁለተኛው በኪራይ ነው፡፡
‹‹ረዘም ላለ ጊዜ ጥናት አካሂደን ሕግ ወደ ማስከበር ገብተናል፤›› ያሉት አቶ ታከለ፣ ኮሚሽኑ ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ የጠረጠራቸውን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉም በተጨማሪ፣ ያልተያዙትን ለመያዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ከኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ ጋር በተያያዘ ዕርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በክልሉና በፌዴራል ደረጃ በርካታ ግንባታዎችን በማካሄድ የሚታወቅ ግዙፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡
ኢንተርፕራይዙ የመጠጥ ውኃ ሥራዎች የማሳያ ግድቦችን ከመገንባቱ በላይ እንደየሁኔታው ስታዲየምና መንገድ ሲገነባ ቆይቷል፡፡ ኢንተርፕራይዙ የተቋቋመው በ500 ሚሊዮን ብር የተከፈለና በሁለት ቢሊዮን ብር የተመዘገበ ካፒታል ነው፡፡
የሪፖርተር ምንጮች በኢንተርፕራይዙ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ግዥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሚሊዮን ብሮች እንደተመዘበረ ቢናገሩም፣ አቶ ታከለ የገንዘቡን መጠን ለጊዜው ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

No comments:
Post a Comment