በተለይ ፖለቲካው ዙሪያ… መተማመን ወይም መታመን ከባድ እየሆነ መጥቷል፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ ለኢህአዴግ የሚሰሩ አባላት (አመራር) አሉ ከሚል
አሉባልታ አንስቶ ስማቸውን እስከመጥቀስ የሚደርሱ ወሬዎችን መስማት የተለመደ
ሆኗል፡፡ ‹እከሌ› ፣‹እከሌ›፣… የተባሉትን ፓርቲዎች ደግሞ ኢህአዴግ ራሱ ነው
የመሰረታቸው ተብለው ተለይተው የሚታወቁ አሉ፡፡ ይህ አይነቱ የመጠራጠር አባዜ
ተቃዋሚ አባላት (አመራር አባላት) እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ብቻ ሳያቆም
የተለያዩ ማህበራት/ ስብስቦች እና ግለሰቦች ላይም ይደርሳል፡፡
ኢህአዴግ ይሄን አያደርግም ብዬ አላስብም፡፡ እንዲያውም ‹አንድም ሁለትም
ሆናችሁ በፖለቲካ ጉዳይ ከተሰበሰባችሁ እኔ በመሃከላችሁ እኖራለሁ› የሚል ውስጥ
ታዋቂ ህግ ሳይኖረውም አይቀርም፡፡ ነገር ግን መለየት መቻል አለብን ኢህአዴግ
በቀደደልን መስመር ገብተን፤ ጥርጣሬያችንን ገደብ አሳጥተን ወይም ምክንያታዊነትን
ገደል ከተን እኛም ተባባሪ እየሆንን እንይሆን እፈራለሁ፡፡
በበኩሌ ‹እከሌ› የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ ወይም የፓርቲ አመራር ወይም አባል
ወይም ተቃዋሚ ኢህአዴግ ነው፣ ለኢህአዴግ ይሰልላል የሚባል ወሬ ሰልችቶኛል፡፡

No comments:
Post a Comment