ከቆራጥ ሙስሊም ወንድሞቻችን ምን እንማራለን?
ህዝበ ሙስሊሙ
ያነሳቸው የመብት ጥያቄዎች ወደጐን በመተው የመንግስት ባለስልጣናት
የሚከተሉትን ህዝብን የማሸማቀቅ አካሄድ መልስ እንዲሆን የተዘጋጀ
ሰነድ “የእምነት ነፃነት ጥሰት መቃወም
ከጀመርን
እነሆ በነዚህ ጊዜያትም ጥያቄዎቻችንን ፍፁም
ሰላማዊ
በሆነ መንገድ እያቀረብን ብንገኝም
ሊሳካልን
የቻለው
ያማረ አካሄድ ማስመዝገባችን
እንጂ ያማረ ውጤትን አይደለም፡፡”
ሲል የአካሄዱን ሰላማዊነት ገምግሟል፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃውሞ መንገድ የተደመሙ የውጭ ሚድያ ና ምሁራን በዝተዋል፡፡
“ከእንግዲህ
የሰላማዊ
ትግል እንቅስቃሴን ለማጥናት የውጭ
መፃህፍትን
ማገላበጥ አያስፈልግም ፤ የሀገሬ
ሙስሊሞች
ሁኔታ ከምንም ይበልጣል” ፡፡ ለዚህ አባባል
መነሻ የሆኑ ሁለት
ምክንያቶችን
ማንሳት
ይቻላል፤ የመጀመሪያው ሀገሪቱ የተደራጀ የሰላማዊ ተቃውሞ ታሪክ
የሌላት
መሆኑ ሲሆን ሌላው ስማቸው
የሽብርተኝነት
ጅሃድና
ብጥብጥ መገለጫ ወደ መምሰሉ ያደላው
ሙስሊሞች ፍፁም ሰላማዊ ሆነው
መንቀሳቀሳቸው
ነው፡፡ “እንደማንም መደዴ ሰው እስልምናን ከጦርነት ጋር ማያያዝ የተለመደ
ነው” የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከዚህ በተቃራኒ
በመንቀሳቀሳቸው
ሁሉንም አስደምሟል፡፡
በአብዛኛው ሀገሮች
አብዮትን
ያስጀመሩ መሪዎች እስከ አብዮቱ ፍፃሜ
አይጓዙም፤የታለመለትን
ግብ የሚመቱ አብዮቶችም እስከዚህም ናቸው፤
አብዛኛዎቹ
አብዮቶች የተደበላለቀ አካሄድ ነበራቸው፡፡ ወቅታዊው የሙስሊሞች
እንቅስቃሴ ከአብዮት በመለስ የተደራጀ በውስጡ በወል የታወቁ
መሪዎች
ያሉት፣
እና ማንም ተነስቶ“ልሙላው
አልሙላው”
የሚለው
አይደለም፡፡
የትኛውም የተቃውሞ
ጎራ ላይ ያለ ቡድን የመጀመሪያው ስራ ሊሆን የሚገባው የሚቃወመውን ወገን ባህሪ ማጥናት
ነው፡፡ ባለፉት 22 ዓመታት
ኢትዮጵያ
ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ይህ
ስራ የጎደላቸው ነበሩ፡፡ በዚህ ወቅት
የዚህን
የቀድሞ
ችግር እየቀረፉ የመጡት የኢትዮጵያ
ሙስሊሞች
ለዚህ ያበቃቸው የመጀመሪያ
ስራቸውን
ያደረጉት ኢህአዴግን በመረዳት ላይ ማድረጋቸው ነው፡፡
ከሀይል በተጨማሪ
መንግስት
በካድሬዎች አስገዳጅነት የተቀነባበሩ የፀረ ተቃውሞ የተቃውሞ
ሰልፎችን
በመላ ሀገሪቱ ማደራጀቱን ማየት ተችሏል፡፡
አንዳንድ
የመንግስት ካድሬዎች ከዚህ እንቅስቃሴ ጀርባ
የሌሉና ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት
ለመቃወም
እንዲወጣ ቢናገሩም አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው“በከሚሴና በደሴና በአዲስ አበባ የተደረጉት `የተቃውሞ`
ሰልፎቹ
መፈክሮች በይዘት አንድ መሆን ብቻ
ሳይሆን
የተፃፈበት ፊደል መጠንም ተመሳሳይ
ነበሩ”፡፡
ከሙስሊሞቹ ተቃውሞ የምንወስደው ትልቁ ትምህርት በምንም ሁኔታ ከሰላማዊነት ያለመውጣት
ነው፡፡ ሰላማዊ ተቃውሞውን
ለማደፍረስና
ሙስሊሙን
ወደ አመፅ ለማምጣት
መንግስት
ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ተቃዋሚዎቹ ወደ
የኃይል አመጽ ያለመምጣታቸው መንግስት
የኃይል እርምጃ ለመውሰድ መንገድ አልሰጠውም፡፡ የሙስሊሞቹ ሌላው አስተማሪ ነገር
አንዱ ደፋር መሆን
ሲሆን ሌላው ቀጣይነት ላለው ጊዜ መቃወም መቻል
ነው፤ አብዛኛው ተቃውሞ በሆነ
አጋጣሚ
ተነስቶ
ወዲያው የሚከስም ነው።
ቀጣይነት
ላለው ጊዜ መቃወም መቻል
ነው ፡፡ ለዚህ
ያበቃው
ደግሞ ዋናው ነገር
ተቃውሞው
ስርዓት
የተዘረጋለት (system) ነው፡፡
የወቅቱን የኢትዮጵያ
ሙስሊሞች ተቃውሞን የተለየ ደረጃ የሰጠው ተለዋጭ የተቃውሞ ስትራቴጂ ማዘጋጀት መቻላቸው ነው፡፡ የተቃውሞን
እንቅስቃሴ
የሚመሩ
ሰዎች የመጀመሪያ ስትራቴጂ
የነበረው
ተቃውሞን መታገስ የማይሆንለትን የኢትዮጵያ መንግስትን በምን
መልኩ ማለፍ እንዳለባቸው ነበር፡፡
እንደ አስተያየት ሰጪዎች ሙስሊሞቹ እንቅስቃሴውን ከሚመሩ
ሰዎች እስከ የተቃውሞ
አካሄድ
ድረስ ሁለተኛና ሦስተኛ አማራጭ ማስቀመጣቸው
ነው፡፡
በተለይ የተቃውሞው አመራሮች ከታሰሩ ሌሎች የሚተኳቸው
ሰዎች ከወዲሁ መመረጣቸው ጉዳዩን በቀላሉ
እንዳላዩት
ያሳያል፡፡
ኢህአዴግ በፈለገው
ቀን እንደበግ እየጎተተ ወደ ወህኒ
የሚወረውራቸው
የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በዚህ መልኩ ከወዲሁ
መተካት
ቢችሉ የተሻለ ይሆናል፡፡ አንድነት ፓርቲዎች መሪዎቻቸው
ሲታሰሩባቸው የተለየ እቅድ ቢኖራቸው
ኖሮ የመጎዳት መጠኑን፡፡ መተካት ያለመቻሉ
የዚሁ “plan B” እጦት ነው፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ
በክብር ለዘላለም ትኑር!
No comments:
Post a Comment