Saturday, August 31, 2013

ሰበር ዜናሰበር ዜና

ሰበር ዜና

ድምፃችን ይሰማ ህዝበ ሙስሊሙን


መንግስትና የሀይማኖቶች ጉባኤ በጋራ በጠሩት ሰልፍ ላይ እንደሚገኝ ድንገታዊ ጥሪ ካስተላለፈ በኋላ በኢሃዴግ ቤት 

ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩ ታወቀ ፡፡

አክራሪነትን ለማውገዝ በሚል መንግስትና የሀይማኖቶች ጉባኤ ለፊታችን እሁድ ነሃሴ 26\2005 በጋራ የጠሩት 


ሰልፍ ላይ ህዝበ ሙስሊሙ እንዲገኝ ድምፃችን ይሰማ መልእክት ካስተላለፈ በኋላ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ሪፖርት 

ለመቀበል ተሰይመው የነበሩ የየክፍለ ከተማ አመራሮች በድንጋጤ ተውጠው ታይተዋል ፡፡

የድምፃችን ይሰማ ውሳኔን ተከትሎ መንግስት መያዝ ስላለበት አቋም ለመነጋገርም ማምሻውን አስቸኳይ ስብሰባ 


መቀመጣቸው የታወቀ ሲሆን በጊዜያዊነት ግን ከዛሬ 10 ፡00 ሰዐት  ሊደረግ የነበረውና ነገ ቅዳሜ ሙሉ ቀን 

ሊደረጉ የነበሩት ጠንካራ የቤት ለቤት ቅድቀሳዎች ባስቸካይ አንዲቆሙ ታዟል፡፡

በተጨማሪም እንዲሁ ሰልፉ በሚካሄድበት እሁድ ጧት ላይ ሰልፈኞችን ወደ ሰልፉ ቦታ የሚያጓጓዙ መኪኖች 


በየወረዳው ተዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም ይህንንም ባልታወቀ ምክንያት እንዲቀር ሆኗል ፡፡

ከዚህ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነሮች ድምፃችን ይሰማ በለቀቀው ውሳኔ ላይ ለመወያየት ማምሻቸወን እስከ 


መሸቱ 2፡ 00 ሰዐት ስብሰባ ላይ እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን የየወረዳና ክፍለ ከተሞች ካቢኔዎችም እንዲሁ 

በተመሳሳይ ሁኔታ ማምሻቸውን በስብሰባ መጠመዳቸው ታውቋል ፡፡

ቀደም ብለው የየወረዳ ሃላፊዎች በሰበሰቡት ስብሰባ ላይም ድምፃችን ይሰማ ይህን ታሪካዊ ሰልፋችንን ሊያበላሽብን 


ነው ሲሉ እንደተደመጡ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡

ሆኖም ድምፃችን ይሰማ ተቃውሞውን ለማበላሸተ ሳይሆን ኢስላም አክራሪነትን አንድንቃወም ስላዘዘን ከማንም 


በፊት ቀድመን መሰለፍ አለብን በማለት መሆኑ የሚታወስ ነው፡፤

ድል ለኢትዬጲያ ሙስሊም!!!

አላሁ አክበር!!!

No comments: