ስለ መንግሥት የቴሌቪዥን ድራማዎች፡-
ሰኞ ነሐሴ 13/2005
በቀዳሚነት መንግስት አሁንም ያሉና የሚታዩ ችግሮችን መፍትሄ ከመሻትና ከመቅረፍ ችግሮቹን በመካድ ቪዲዮዎችን አቀነባብሮ ብቻ ወደ ሕዝብ በመልቀቅ ህብረተሰቡን ለማታለል ጥረት ማድረግ ምርጫው ማድረጉ እንደ አንድ የኅብረተሰብ ክፍል በጣም ያሳስበናል፡፡ ከዚህ ቀድም እንደነበሩት ሁሉ ታሳሪዎች ከፍርድ ቤት ውሳኔ በፊት ነጻ ሆኖ የመገመት መብታቸውን በመንጠቅ፣ በሕግ ጥላ ስር ያሉ ታሳሪዎችን መንግስት በሚፈልገው መልኩ በማናዘዝ የሚሻውን በሚዲያ እንዲሉለት ማድረግ መቀጠሉ የችግሩን ቁልፍ አንደማይፈታው እሙን ነው፡፡
የሕዝብ ሐብት ሊሆን የሚገባው ብሔራዊ ቴሊቪዥንና ሌሎች በመንግስት ይዞታ ስር ያሉ ሚዲያዎች በድብደባ የደከሙ ታሳሪዎች ኑዛዜዎች ቆርጦ በመቀጠልና በማቀናበር ያላቸውን ‹‹ልምድ›› በመጠቀም የሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች የኅብረተሰቡን ችግር ከመፍታት ይልቅ በሕዝቡ ውስጥ ቂምና እልህ እንዲበረታ እያደረገው ነው፡፡ ለካሜራ እንደሚፈለገው ‹‹ፈገግና ፈታ ብለህ አላወራህም›› እየተባለ በድብደባ የሚሰራው የምርመራ ክፍል ድራማ ሕዝብን ፈጽሞ ሊያታልል አይችልም፡፡ መንግስት ለመንፈቅ ያህል በለፋበት ‹‹ጂሐዳዊ ሐረካት›› ድራማ መታየት ማግስት የታየውን የህዝብ እልህና ቁርጠኝነት ማስታወስ ብቻ ፊልም ማቀናበር መፍትሄ አንደማይሆን ለማገናዘብ በቂ ነበር፡፡ መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በማስመልከት ያፈሰሰው የፕሮፖጋንዳ ኢንቨስትመንት ውጤቱ ዜሮ ብቻ መሆኑን አሁን ያለውን ሁኔታ ብቻ መመልከት በቂ ነው፡፡ ‹‹የሸሪአ መንግስት ለመመስረት የሚፈልጉ ኃይሎች›› የሚለው ተረት ከተጣለበት ቦታ ተነስቶ እንደ አዲስ የሚራገበው ቀድሞውንም አሳመኝ ሳይሆን ቀርቶ መጣሉን ማስተዋል ተስኗቸዋል፡፡
የተሰሩ የፕሮፖጋንዳ ናዳዎች ሁሉ የመንግስት ተአማኒነት ሸርሽረው ወሰዱት እንጂ ይህ ነው የሚባል ጥቅም ሊሰጡት አልቻሉም፡፡ በጣም በሚያሳዝን መልኩ መሪዎቻችን ከዚህ ቀደም ያለ ፈቃዳቸው እንዲሁም ሕገ መንግስቱን በመጣረስ፣ የፍርድ ቤቱንም ትእዛዝ በመተላለፍ ራሳቸውን ወንጀለኛ አድርገው እንዲቀርቡ ተገደው የነበረበትን ትእይንት መንግስት እንደ አዲስ አሁንም አሳይቶናል፤ መንግስት ከሕግ በላይ መሆኑንም በተገቢው መልኩ መልእክት እያስተላለፈልን ነው፡፡ የሕግ የበላይነት ማረጋጋጫ የሆነው የተጠርጣሪዎች ከፍርድ በፌት ነጻ ሆኖ የመታየት መብት ተደጋግሞ እየተሸረሸረ አይተነዋል፡፡ ...

No comments:
Post a Comment