Monday, August 19, 2013

በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ቀውስ ተከትሎ የተፈጠረው የሃይል ሚዛን የስብሃት ነጋ ቡድን ያነጣጠረው

በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረውን የውስጥ ቀውስ ተከትሎ የተፈጠረው የሃይል 

ሚዛን የስብሃት ነጋ ቡድን ያነጣጠረው

1- ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከኤፈርት መሰስ ብለው እንዲወጡ እንደተደረገው በሕወሓት ውስጥ ያላቸውንም ቦታ እና በማእከላዊ መንግስት በኩል የተሰጣቸውን ክብር በማውረድ ደንግጠው እንዲቀመጡ ከተቻለ ከአገር ውልቅ ብለው ወተው ድምጻቸውን ሳያሰሙ እንዲኖሩ ካልተቻለ በሙስና ተይዘው አደባባይ ላይ እንዲጋለጡ ይደረጋል::ይህ የሚሆነው ፖለቲካውን ማቡካት ካላቆሙ ነው::

2-አቶ በረከት ስምኦን በሃገሪቱ ውስጥ ያለቸውን ሃይል እና በፓርቲው ውስጥ ያላቸውን የተደማጭነት ጉልበት እንዲያጡ ይደረጋል:: በፖለቲካ ማምታታቶች ባገነፈሉት እሳት ይዘፈቃሉ::አቶ በረከት ላይ የስበሃት ነጋ ቡድን የከፈተው ዘመቻ እንደሚያሳየው ግለሰቡ የስልጣን የበላይነት የሚናፍቅ የትግራይ ህዝብን እና ሕወሓትን የሚጠላ ተደርጎ እንዲወሰድ እየተሮጠ ነው::
በትግራይ ህዝብ እና በተዳከመው የወያኔው ድርጅት መካከል የአለቃውን መርዝ በመርጨት የስበሃት ነጋን ቡድን አፈር ለመክተት እየሰራ መሆኑ ተደርሶበታል::አንድ እውነት አለ በረከት ስምኦን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ረዥም ጊዜ አይቆይም::

3-ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በጡራታ ማባረር ወይንም በጤንነት ችግር ምክንያት አድርጎ ስልጣን እንዲለቅ ማድረግ በምትኩም ወታደራዊ ልምድ ያለውንእና የሰለጠነ የህግ ሰው የሆነውን ጄኔራል አበበ ተክለሃይማኖትን በመሾም የወታደሩን ክንፍ መቆጣጠር::

4-አቶ አባይ ወልዱ በቂ እውቀት የለለው እና በመለስ ራእይ ስም እየነገደ በስልጣን መቆየት የሚፈልግ ለትግራይ እና ለትግራይ ህዝብ ምንም የማይፈይድ የእውር ድንብር ስለሆነ ከስልታን ይባረራል አርፎ የማይቀመጥ ከሆነ በሙስና ይገባል:: ከሃገር መውጣት አይፈቀድለትም ::

በእነዚህ እና በሌሎች የበረከት ስምኦን ቲፎዞዎች ላይ በ አቶ ጌታቸው የሚመራ የደህንነት መዋቅር ከፍተኛውን ጥናት እና ክትትር እያደረገ መሆኑን ምንጮቹ ውጥረቱን ጫፉን ተናግረዋል::
— at ምንልክ ሳልሳዊ .

No comments: