ነፃነትና ሕግ
"ፍፁማዊ ስርዓትን የተነተኑት ዶ/ር ዳኛቸው ይሄው ስርዓት ከነፃነትና ከሕግ ጋር ስላለው ግንኙነትም ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ነፃነትና ሕግ በጣም ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸውን በሰፊው አውስተዋል። ሕግና ነፃነት ወይም ነፃነትና ሕግ ያላቸው ዝምድና እንዲሁም ከህግ የበላይነት (Rule of law) ወደ Rule by law ‘‘ሕግ እያወጡ ማሸት’’ እያነፃፀሩ አሳይተዋል።
ሕግ እያወጡ መግዛት (Rule by law)
የተወሰኑ ሰዎች እንደፈለጉ ሕግ እያወጡ ‘‘ተከተለኝ’’ ማለት ሲሆን የህግ የበላይነት (Rule of law) ግን በህግ መመራት መሆኑን አብራርተዋል።
ዶ/ር ዳኛቸው ነፃነትና ሕግ ያላቸውን ግንኙነት ሲያብራሩ ያለሕግ ነፃነት እንደሌለ ገልፀዋል። ሕግ በውስጡ ትእዛዝ ብቻ ሳይሆን መብትና ፍትህ ያዘለ መሆን አለበት ብለዋል። ትልቁ የእንግሊዝ ፈላስፋው ጆን ሎክ “ስልጣን በአንድ ቦታ ከተከማቸ በዚያው መጠን ነፃነት ይሞታል” ማለቱንም አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ የሕግ ታሪክ በአቶ አበራ ጀምበሬ መጠናቱን ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሕግ ዝም ብሎ ትእዛዝ አይደለም። ሕግ ሰዎች በር ዘግተው የሚያወጡት ትእዛዝ አይደለም። ሕግ መብት የሚል ፅንሰ ሐሳብ አለው። ፍትሕ ከሚባለው ነገር ጋራ አብሮ ተጣምሮ የሚገለጽ ነገር ነው። በኢትዮጵያ በሕግ አምላክ ሲባል ሕግ ፍትሕን ማቀፉን ያመለክታል። ‘‘ሕጉ ይከለክላል’’ ሲባል ፓርላማ ያወጣው ሕግ ማለት ብቻ አይደለም።
አሁን ሕግ መብት ፍትህ የሚለው ቀርቶ ሰዎች አንድ ቦታ ተሰብስበው የሚያወጡት ትእዛዝ ሆነ፤ እነ እገሌ… አሸባሪ ናቸው እየተባለ ሕግ ይወጣል። የውጭውን መሬት ሸጬ ጨርሻለሁ አሁን ደግሞ የግቢህን እሸጣለሁ የሚል ሕግ ይወጣል፤ የኻያ አራት ወይም የኻያ አምስት ዓመት ወጣት ርእዮት የምትባል ትንሽ ልጅ አነበበች ነው ምናምን ተብሎ 14 አመት ሽብርተኛ ተብላ ይፈረድባታል። ታዲያ ይሄ ሕግ ፍትህ አለው?’’ ሲሉ በመጠየቅ በሀገራችን ላይ ሕግና ነፃነት የተራራቁ ሆነዋል። ሕጉ አለ ብለን እንቅልፍ እንዲወስደን ነበር ነገር ግን ሕጉ ጥበቃ ሊያደርግልን አልቻለም። ምክንያቱም ከሰዋዊ ሥልጣን አልተላቀቅንም (Power depersonalized) መሆን አልቻለም። የሕግ አመራር (Rule by law) ሳይሆን የሰው አመራር ነው ያለው ብለዋል።
ፍትህና ህግ እየተጋጩ መሆኑንም ዶ/ር ዳኛቸው አብራርተዋል። ፍትሃዊ ያልሆነ ሕግ፤ ሕግ አይደለም ብለዋል ‘Just Law’ እና ‘Unjust Law’ የሚባል ነገር እንዳለም አብራርተዋል። ማርቲን ሉተር ኪንግ ታስሮ አንድ ቄስ ‘‘አንተ ሰላማዊ ሰልፍ እያስወጣህ ሕግ እየሰበርክ ነው’’ አሉት እሱ በበኩሉ ‘‘እኔ ሕግ ሰባሪ አይደለሁም። እርስዎም ሆኑ እኔ ሴንት ኦገስቲንን አንብበናል። ‘Just Law’ የሚባል ነገር አለ Unjust Law የሚባል ነገር አለ። እኔ እየተቃወምኩ ያለሁት ዘረኛውን (Unjust Law)ን ነው። Unjust Law ደግሞ ሄዶ ሄዶ ህግ አይደለም አላቸው። እና ሕግ ዝምብለው ሰዎች የደነገጉት ትእዛዝ ማለት አይደለም። ቢያንስ ፍትሃዊ መሆን አለበት። ሂትለርም ሕግ እያወጣ ነበር የሚያሻው። እና አሁንም ሕገ መንግስቱን ተፃራችኋል፣ ሕጉ አይፈቅድም የሚባለው የሕግ Fetish (ልክፍት) ነውያለው’’ ብለዋል።"

No comments:
Post a Comment