አና ጎሜሽ Ana Gomes [አሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ እአአ 2005/AP Photo]
“ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ትናንት በአውሮፓ ፓርላማ የተካሄደው ውይይትና ክርክር በጣም ጥሩ እንደነበር የገለጹት የፓርላማው አባል ሚስ አና ጎሜሽ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በስብሰባው ላይ የተገኙት በአውሮፓ ፓርላማ አባላት ተጋብዘው መኾኑንም አረጋግጠዋል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
የአውሮፓ ሕብረት አባል እና በኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ 97 የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢ ቡድንን የመሩት ሚስ አና ጎሜሽ “ድርቅና ረሃብ በኢትዮጵያ” (Famine and Drought in Ethiopia) በሚል አሁን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ረሃብ በትናንትናው ዕለት በቤልጅየም ብራስልስ በአውሮፓ ፓርላማ ፊት የተካሄደው ውይይት እና ክርክር ጥሩ እንደነበር ገለጹ፡፡
እንደ ሚስ አና ጎሜሽ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቤልጅየም ብራስልስ ተገኝተው በአውሮፓ ፓርላማ ትገኝተው ለአውሮፓ ኮሚሽን የውጭ ጉዳዮች አገልግሎት (European External Action Service /EEAS) ገለጻ እንዲያደርጉ እንደጋበዟቸውና በግብዣውም አማካኝነት ተገኝተው ሰፊ ገለጻ እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡
ጽዮን ግርማ ሚስ አና ጎሜሽን አነጋግራ ያጠናከርችውን ዘገባ ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡
http://m.amharic.voanews.com/a/ana-gomes-responds-on-eu-invitation-of-berhanu-nega/3084918.html
No comments:
Post a Comment