Wednesday, May 6, 2015

የሰማያዊ ፓርቲው ማቲያስ መኩሪያ ድብደባ እየተፈፀመት ነው

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ሰበብ ሚያዝያ 26/2007 ዓ.ም ቤቱ ውስጥ እያለ ተይዞ የታሰረው ማቲያስ መኩሪያ በደህንነቶች ድብደባ እየተፈፀመበት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ማቲያስ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት የተደረገ ሲሆን ከሌሎች እስረኞች ተለይቶ እንዲታሰርም ተደርጓል፡፡ በታሰረበት ቀን ማታ ታስሮበት ከነበረው ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ወዳልታወቀ ቦታ ወስደውት የነበር ሲሆን ሲመለስም ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት እንደተመለከቱ እስረኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

No comments: