Wednesday, May 6, 2015

ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው ~ የፈረንሳይ ለጋስዮን ወጣቶች

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ላጋስዮን ወረዳ 2 የሚገኙ ወጣቶች ማታ ማታ በወረዳው የወያኔ ካድሬዎች ጥቆማ ተልቅመው እየታሰሩ ይገኛሉ። ወጣቶቹ ከአቅማችን በላይ እየሆነ ነው ይላሉ። እስካሁን ብዙ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስ ታፍሰው የታሰሩ ሲሆን የደረሱበት አልታወቀም። ከእስር በተጨማሪ ካድሬዎቹ ለወያኔ/ኢህአዴግ ህዝቡን እንዲመርጥ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ድብደባም እየፈፀሙ መሆኑን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

መብታችን እስካልተከበረ ድረስ ሁላችንም ወህኒ ቤት ባንሆንም እስረኛ መሆናችንን ተገንዝበን ወያኔን ለማስወገድና ዲሞክራቲክ መንግስት ለማቋቋም ልዩነታችን ወደ ጎን ትተን አንድነታችን በማጠናከር እንታገል ስል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

No comments: