የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ሚያዝያ 27/2007 ዓ.ም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብትና ሰራተኞች ምክትል ዋና ፀኃፊ የሆኑት ሚስተር ስቲቭ ፌልድስቴይን ጨምሮ ሌሎችንም ኃላፊዎች አግኝተው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ቀጠናው ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡
ኢ/ር ይልቃል ከስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ መጭው ምርጫ፣ ሰብአዊ መብት አያያዝ፣ የእምነት እና ሀሳብን በነፃነት መግለጽ መብት፣ ሲቪክ ማህበረሰብ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በፀረ ሽብር ህጉና በደህንነት ስም እየተፈፀሙ ያሉ ችግሮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ ሚስተር ፌልድስቴይን ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እንቅስቃሴዎች ዝርዝር ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ኢ/ር ይልቃልም በዝርዝር ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡ በቅርቡ ምክትል የውጭ ጉዳይ ኃላፊዋ ውይንዲ ሸርማን ንግግር ላይም መወያየታቸው ታውቋል፡፡

No comments:
Post a Comment