Monday, May 4, 2015

ገዢው ፓርቲ ህዝቡ በቡድን ድምጽ እንዲሰጥ እያዘጋጀ ነው

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው ምርጫ ላይ ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል።
ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው።
የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየመሩ በመውሰድ ፣ ድምጻቸውን ለኢህአዴግ መስጠታቸውን ያረጋግጣሉ።
የአንድ ለአምስት ጠርናፊ ስለአባላቱ የቀን ተቀን ህይወት መረጃዎችን እየሰበሰበ ሪፖርት ካቀረበ በሁዋላ፣ በእለቱ አባላቾ ድምቻውን ለኢህአዴግ መስጠታቸውን ያረጋግጣል። የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ህብረት አይታዘበውም።
Source: Esat

No comments: