(ደስታና ሐዘን ~ 27 ወጣቶች ከሊቢያ ወደ ካይሮ ገቡ፣ 21 ወጣቶች ከኢትዮጵያ ተሰደው ጅቡቲ ገቡ!)
በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ የሚመጣብኝ ሰው ለኔ ምንም ሊሆነኝ አይችልም። ሃገርና ህዝብ ለያይቶ ማየት አይቻልም። ሁለቱም ለኔ የማንነቴ መገለጫ ናቸው። ሃገር ወዶ ህዝብን መጥላት ወይንም ህዝብን ወዶ ሃገርን መጥላት ለኔ አይቻለኝም።
ወደ ተነሳሁበት ዋናው ነጥብ ስመለስ ዛሬ በወገኖቼ ላይ እየደረሰ ባለው ነገር የደስታና የሃዘን ስሜት እያስተናገድኩ ለመዋል ተገድጃለሁ። ደስታው በሊቢያ በደህንነት ሃይሎች ተይዘው የነበሩት 27 ወጣቶች በግብፅ ተደራዳሪነት ተፈተው ግብፅ ካይሮ መግባታቸውና የግብፁ ፕሬዚዳንት አል ሲሲ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በመሆን አይሮፕላን ማረፊያ ድረስ ሄደው መቀበላቸውን ተከትሎ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ነፍስ ዝም ብሎ እያለቀ ባለበት በዚህች አስከፊ ወቅትና የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ ባይ ወያኔ ለወገኖቻችን ማድረግ እሚጠበቅበት ካለማድረጉም በላይ ለወገኖቻችን ለመድረስ በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ በሚገኝበይ ሰዓት የግብፅ መንግስት ወገኖቻችን ለማዳን ያደረገው ቀናነት ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል።
ደስታ ላይ ሆኜ ሃዘንም ውስጥ ነኝ! ይህም የሆነበት ምክንያት እንደሚከተለው አንድ ሁለት ብዬ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ:-
1. ባለፈው ጊዜ በሜዲትራኒያን ባህር በሰጠመው ጀልባ ከሞቱት 700 ስደተኞች 10 ወጣቶች ከአንድ ሰፈር የወጡ የጎጃም በረንዳ(አባኮስትር ሰፈር) ልጆች መሆናቸው
2. የጎረቤት ሃገራት በችግር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ወጥቶች ለማዳን በሚረባረቡበት በዚህ ወቅት ወያኔ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ መቀጠሉ ነው። በዚህም የወያኔ አፈሳ ለማምለጥ ሲሉ ለስደት እየተዳረጉ ያሉ ወጣቶች መበራከቱ ነው። አሁን በደረሰኝ መረጃ ከፈረንሳይ ለጋስዮን ብቻ 21 ወጣቶች ወደ ሳውድ አረቢያ ለመሄድ ጅቡቲ ገብተዋል። ሌሎች ስደት ላይ ያሉትን ለማዳን ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚች ቀውጢ ወቅት ወያኔ ወጣቶችን በማሸበር ለስደት እየዳረጋቸው ይገኛል።
3. ምንም እንኳን ከሊቢያ 27 ወጣቶች ካይሮ ቢገቡም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ችግር ላይ መሆናቸውን ነው። በየመን ከ2000 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ቢመዘገቡም የወያኔ መንግስት ግን አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርግላቸው አልቻለም።
4.........
እኔ ደስታና ሃዘን ውስጥ ነኝ! ግራ የሚያጋባ ወቅት!
እኔ ደስታና ሃዘን ውስጥ ነኝ! ግራ የሚያጋባ ወቅት!
ወገኖቼ ስደት አቁመን የችግራችን መንስዔ የሆነውን ወያኔን ለማስወገድ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናል። ስደት ለሃገራችንና ለህዝባችን መፍትሄ ሊሆን አይችልም! ቆም ብለን እናስብ! የችግሩ ባለቤትም መፍትሄም እኛው መሆናችን ለሁላችንም ግልፅ ሊሆን ይገባል!
ግብፅ በወያኔ መንግስት ያለተገኘውን ለወገኖቻችን ላደረገችው የነፍስ አድን ስራ ልትደነቅና ልትመሰገን ይገባል!
ቸር ሁኑልኝ!
ስዩም ወርቅነህ
No comments:
Post a Comment