Monday, August 19, 2013

ይድረስ! ለቀድሞውና ለአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትሬ፣ ድንጋዩን ዳቦ ላደረጉትና የድሆች አባት እንዲሁም ባለራዕዩ ለሆኑት መለስ ዜናዊ........
መቼም አንባቢ ነዎትና በርዕሱ መርዘም አይበሳጩብኝም! ጠመንጃ ተንተርሰው ያነቡ(እቺን ቃል ጠበቅ አድርገው ያንብቧት ጌታዬ-ኋላ እንዳይቀየሙኝ) የነበረ ሰው፣ እንዴት ክንድዎን ተንተርሰው ይህችን ለማንበብ ይሰንፋሉ ተብሎ ይጠረጠራል? እንደውም እንደኔ ስንፍና አሳጠርኩት እንጂ፣ እንደ እርሶ ብርታትስ ቢሆን ከዚህ ሰባት እጅ በረዘመ ነበር

...ግን እንዴት አሉልኝ አባቴ? አባቴ የምሎት ሙልጭ ያልኩ ቺስታ በመሆኔና “የደሀ አባት” መሆንዎን ስለሰማሁ ነው፡፡ የድሃ አባት መሆንዎን የሰማሁ ቀን እንዴት ነበር የተደሰትኩት! ቀድሞውንም አባቴ ጥሎኝ የሄደው በልጅነቴ ነበር፣ ድህነቴን ሳይንቁ አባቴ መሆንዎን ስሰማ፣ ደስታ መሰሎት የተደሰትኩት... በቃ ጥሎኝ የጠፋው አባቴ እሳቸው ናቸው አልኩ! አባቴ ትቶኝ የሄደው ገና ነብስ ሳላውቅ ስለነበር፣ ጫካ ገብቶ ሊሆን እንደሚችል፣ ልጄን ብሎ ያልፈለገኝ ትግሉ ፋታ አልሰጥ ብሎት እንጂ፣ ጨክኖብኝ እንዳልሆነና እርሶ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠረጠርኩ፡፡ በዛ ላይ አንዳንድ የሰፈሬ ሰዎች ሲያዩኝ፣ “ይሄ ልጅ ግን እሳቸውን አይመስልም?” ሲሉ ስሰማማ ይተዉኝ አልኮት... ታዲያ ሰሞኑን ሌላኛዋ ልጅዎ የሆነችው “ስምሃል”፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ባንክ እንዳስቀመጠች ብሰማ ጊዜ፣ “እንደሚባለው የድሆች አባት አይሆኑ ይሆን?” የሚል ክፉ ጥርጣሬ ልቤ ገብቶ ሰላም ሲነሳኝ አልሰነበተም መሰልዎ! ታዲያ መልሱን እራሴ አገኘሁትና ትንሽ እፎይ አልኩ፡፡ “ድንጋይን ዳቦ ያደረጉ መሪ” እንዴት የደሃም የሃብታምም አባት መሆን ያቅታቸዋል? አልኩ፡፡
ቀድሞውንም — with Hanna Metasebia

No comments: