Tuesday, August 13, 2013

ባንዲራ ቀደዳችሁ፣ ባንዲራ አቃጠላችሁ አይደል እናንተ አክራሪ እና ፅንፈኛ ሙስሊሞች ለሚሉ ወገኖች የተሰጠ ምላሽ::

ባንዲራ ቀደዳችሁ፣ ባንዲራ አቃጠላችሁ አይደል እናንተ አክራሪ እና ፅንፈኛ ሙስሊሞች ለሚሉ ወገኖች የተሰጠ ምላሽ::

አቡዳወድ ኡስማን

በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዬጲያ ሙስሊሞች የኢትዬጲያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርጎ ለማውለብለብ በጠላት በተቃጣብ ጦርነቶች ሁሉ ከሌላው እምነት ጋር በመሰለፍ ዳር ድንበራችንን ስናስከብር እና ደማችንን ለባንዲራችንን ክብር እና ለሃገራችንን ስንል ስናፈስ መቆየታችንን የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ደግሞ በማንም የሚካድ አይደለም፡፡

በኢቲ በቀረበው ዘገባ መሰረት አክራሪዎች ባንዲራ ሲያቃጥሉ ነበር በማለት ዘገባ ሰርቷል፡፡ በዚህ ዘገባ ላይ ባንዲራ ሲያቃጥል ወይም አሮጌ በዝናብ እና በጸሃይ መፈራረቅ የተቀዳደደ ባንዲራ ይዞ ሲያውለበልብ አሳይቷል፡፤በዚህም በመነሳት እዛ መስጂድ ላይ በቦታው የነበሩትን በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች አክራሪዎች እና ፅንፈኞች በማለት ሰላማዊ የመብት ጠያቂውን ዜጋ ስም ለማጥፋት ሞክረዋል፡፡

እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንጠይቃቸው

1.
ባንዲራው በወቅቱ ተቃጥሎ ነበር ብለን እንቀበላቸው እና ኢቲቪ ይህን ድርጊት ሲሰራ በቪዲዬ ቀርፆ ዝም ከሚል የተቀደደው እና የተቃጠለው የሃገር ባንዲራ ነውና በአቅራቢያው የጦር መሳሪያ ታጥቀው በመቶ ሺዎች የሚቆጠረውን ሰላማዊ የመብት ጠያቂ ህዝበ ሙስሊም ከበው ቆመው ለነበሩ ፌደራል ፖሊሶች ለምን ወንጀለኛው በቁጥጥር ሲር እነዲያውሉት ጥቆማመውን አላደረሰም???? በየትኛውም ህግ መሰረት ወንጀል ሲሰራ አይቶ ዝም ያለ እራሱ ወንጀለኛ ነው ይላል፡፡

2.
በአካባበው ያሁሉ ሺህ የፌደራል ፖሊስ የጦር አውድማ እስኪመስል ድረስ ከነሙሉ ትጥቃቸው ህዝበ ሙስሊሙን ከበው ጥበቃ ሲያካሂዱ ስለነበር ለምን ይህን የመሰለ የሃገርን ክብር የሚያዋርድ አጸያፊ ተግባር ሲፈጸም ከነበረ ስለምን ዝም ብለው ተመለከቱት ???
ወንጀል ሲሰራ አይቶ ዝም ያለ እራሱም የወንጀሉ ተባባሪ በመሆኑ በህግ ሊጠየቅ ይገባዋል::

3.
እንደ አንድ የሃገር መንግስት ይህ ድርጊት ተፈፅሞ ከሆነ ወንጀለኛውን ለምን አስካሁን በቁጥጥር ስር አውሎ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት አልፈለገም????? ወይስ መንግስት ሆደ ሰፊ ስለሆነ የሃገር ክብር የሆነውን ባንዲራ ሲዋረድ ዝም ብሎ ተቀመጠ?????

4.
መንግስት አንድ ሌባ መርፌ ሲሰርቅ እጅ ከፍንጅ ከያዘው ለፍርድ እንደሚያቀርበው የሚታወቅ ሲሆን የዚህ መሰሉ ከባድ ወንጀል ሲፈፀም ተመልክቶ በዝምታ ካለፈ ቡሃላ ወቅት ጠብቆ 2 አመት ያስቆጠረውን የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ ሃይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ሌላ ገፅታ እንዳለው አድርጎ አስመስሎ በማቅረብ ለምን እንደ አዲስ ለፕሮፖጋንዳ ተጠቀመበት???? ለምንስ ድርጊቱ በተፈጸመ ምሽት በዜና መልክ አላቀረበውም????

5.
ወንጀለኛው ምስሉ በቪዲዬ ተቀርፆ ካሳዩን ቡሃላ አልተያዘም ግለሰቡ ብሎ ከማፌዝ አይደለም በቪዲዬ ምስሉ እና የፈጸመው ወንጀል መረጃ ኖሮበት ይቅርናጀግናውየኢትዬጲያ የመረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ጥምር ቡድን በርካታ ሽብርተኞችን ተከታትሎ በውስጥ መስመር መያዡን ሁሌ ያበስረን እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ታዲያ ምነው አሁን ጥቂትም ሊባል የማይችለውን ይህን አንድ ግለሰብ ያውም አዲስ አበባ ከተማ ላይ ያውም መሃል ከተማ ላይ ይህን አጻያፊ ወንጀል መፈፀሙን እየተመለከተ ለምን መያዝ ተሳናው፡?????

6.
ባንዲራ ተቃጠለ ተብሎ ህዝበ ሙስሊሙ የሰማው በኢቲቪ እንጂ በቦታው የነበረ አንድም ሙስሊም ባንዲራ ስለመቃጠሉ የሚያውቀው ጉዳይ አልነበረም፡፡በትክክልም ባንዲራ በመቶሺዎች በሚቆጠሩ ሙስሊሞች ፊት ተቃጥሎ ቢሆን ኖሮ ህዝበ ሙስሊሙ የተካሄደውን ወንጀል ከማውገዝም አልፎ ድርጊቱን ፈፃሚውን ለፖሊስ አሳልፎ ከመስጠት አይቆጠብም ነበር፡፡ ምክንያቱም የቆመለት አላማ ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አጀንዳ ስላልሆነ፡

፤በዚሁ ቀንም ኢቲቪ በምሽት ዜናው ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ ተካሂዶ የነበረውን በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ፒያሳን አጥለቅልቀው በተሳተፉበትን ፍፁም አስደማሚና ሰላማዊ ተቃውሞ በመርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጀድ እንደተካሄደ በማስመሰል ሁከት እና ብጥብጥ እንደተፈጠረ አድርጎ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡ ከመቼ ጀምሮ ነው ፒያሳ እና መርካቶ በአንድ መጠሪያ መጠራት የጀመሩት ??? ፒያሳ እና መርካቶን አቀያይሮ ለፕሮፖጋንዳው ሲል በኢቲቪ ያቀረበው መንግስት ባንዲራም አቃጥለው ነበር ብሎ ከጊዜያት ቡሃላ ዜና ቢሰራ ምኑ ይገርማል ???

ከሁሉም የሚያስደንቀው ግን በወቅቱ መርካቶ በሚገኘው በታላቁ አንዋር መስጂድ አንዲትም የተቃውሞ ድምፅ ያልተሰማ ሲሆን መንግስት ግን በዛው ዕለት በታላቁ አንዋር መስጂድ አሮጌ ባንዲራ አንድ ግለሰብ በተቃውሞ ላይ ሲያውለበልብ እንደነበር በማስመሰል አቀረበ እንጂ ባንዲራ ስለመቃጠሉ በዛ ምሽት ላይ ዘገባ አላቀረበም ነበር፡፡ ያቀረበውም ዘገባ ፒያሳ እና መርካቶን በመቀያየር በመርካቶ ውስጥ ሁከት እና ረብሻ ተፈጥሮ አንደነበር በማስመሰል ብቻ ነው፡፤

7
ለሁለት አመታት መርካቶ በሚገኘው በታላቁ አንዋር መስጂድ ተመሳሳይ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲካሄድ በሃገር ውስጥ የሚታተሙ ጋዜጦች እና የውጪ ሚዲያዎች ሰላማዊነቱን አድንቀው ሲዘግቡት ይህን ሳይዘግብ የከረመው .. ግን በሁለት አመቱ ፒያሳ በሚገኘው ኑር መስጂድ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲካሄድ መርካቶ አንደተካሄደ እና እንደተረበሸ አድረጎ ማቅረቡ እንዲሁም ሳምንታት ካለፉ ቡሃላ እንደአዲስ ባንዲራም አቃጥለው ነበር ብሎ ማቅረቡ ድራማ መሆኑን አያሣይምን???? ኢቲቪ ባንዲራው ሲቃጠል ቀርፆት ከነበረ በዕለቱ ረብሻ ተፈጥሮ ነበር ባለበት ዜናው ላይ ለምን አያይዞ አላቀረበውም ????

8.
ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ቦታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ከአርብ ፀሎት ቡሃላ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም ለመጠየቅ ተሰባስበው የነበረ በመሆኑ አንድ ግለሰብ በፈጸመው ተግባር እንዴት ያን ሁሉ ሺህ ህዝብ መወንጀል ይቻላል???? ያንን ያረጀ ባንዲራ አንድ ግለሰብ እንጂ ሁለት እና ሶስት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች ይዘው ሲያውለበልቡ አልተገኘም ፡፡ አንድ ግለሰብ ከመቼ ጀምሮ ነው ህዝብን መወከል የሚችለው??? ለምሳሌ አንድ የክርስትና እምነት ተከታይ እሁድ ቀን ተክለሃይማኖት /ክርስቲያን ውስጥ ያረጀ ባንዲራ ይዞ ቢገባና ቢያውለበልብ ህዝበ ክርስቲያኑን በሙላ በዚህ ሰው ድርጊት መወንጀል እንችላለን?????

9.
በባህር ዳር ከተማ አንድ ጥጋበኛ ፌደራል ፖሊስ መንግስት ህዝብን ከወንጀለኞች እንዲጠብቅበት ባስታጠቀው መሳሪያ 16 የሚጠጉ ንፁሃን ሰዎችን በመሳሪያው ደብድቦ ሲገድል ለምን የፌደራል ፖሊሶች በሙሉ አሸባሪ፣ፅንፈኛ፣ወንጀለኛ አልተባሉም???? በወቅቱ ይህን ድርጊት ሲፈፅም ሌሎች የፌደራል ፖሊሶች በአካባቢው ከነትጥቃቸው ቆመው ሲመለከቱት ነበር፡፡ ለምን ወንጀለኛ ተብለው አልተፈረጁም???? ወይስ ጅምላ ፍረጃ ለህዝብ እንጂ ለመንግስት አይሰራም????

10.
ህዝበ ሙስሊሙ ባንዲራ መቅደድ እና ማቃጠል አላማው ከሆነ ለምን ለድፍን ሁለት አመታት ተቃውሞ ሲያሰማ ለምን ባንዲራ አላቃጠልም???

11.
ህዝበ ሙስሊሙ የባንዲራ ጠላት ከሆነ በዘንድሮ በኢድ በአል ቀን በስታዲም ያሁሉ ምዕመናን ባንዲራ ለብሶ እና ባንዲራ እያውለበለበ በአሉን ሊያከብር ለምንስ መጣ ???? የመንግስትን ጣልቃ ገብነት በሰላማዊ መንገድ ሲቃወሙ ሙሉ በሙሉ በኢትዬጲያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ነበር፡፡ ሆኖም ለባንዲራ ክብር አለኝ የሚለው መንግስት የላካቸው የፌደራል ፖሊሶች ለባንዲራ ክብር እንኳን ብለው ሳይራሩ ያንሁላ ለበአል ስታዲየም የወጣውን ህዝበ ሙስሊም አሸባሪ እያሉ ለምን ደበደቡ?????

12.
አንድ ግለሰብ የሰራው ተግባር ሁሉንም በቦታው የነበሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ወንጀለኛ ካስደረገ ሟች /ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ባንዲራ ጨርቅ ነው ብለው የባንዲራን ክብር ሲያዋርዱ ለምን የወከሉትን ህዝብ እና ፓርቲ ወንጀለኛ አላደረግናቸውም?????

13.
ሟች /ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ከኬኒያ እና ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ጋር ሆነው ሁሉም የሃገራቸውን ባንዲራ ከፍ አድርገው ሲያውለብቡ የኛው /ሚኒስተር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ግን ባንዲራውን ዘቅዝቀው ነበር ሲያውለበልቡ የነበረው፡፤ በህጉ ደግሞ ባንዲራን ዘቅዝቆ ማውለብለብ ወንጀል ነው፡፤ የባንዲራን ክብር እንደማጉደፍ ነው የሚቆጠረው፡፡ታዲያ ምነው እኝህን መሪ ለምን አክራሪ ጸረ ኢትዬጲያዊ አልተባሉም???? አለማወቅ ከህግ ቅጣት እንደማያድን የታወቀ ነው፡፤

በዚህ አለም አቀፍ ሚዲያዎች በተገኙበት ቦታ ላይ ሁሉም መሪዎች ሰንደቅ አላማቸውን ከፍ አድርገው ሲያውለበልቡ የኛው መሪ የነበሩት ግን ዘቅዝቀው ማውለብለባቸው ሳያውቁ ነው ያስብላልን ???

የዚህን መሰል አለም አቀፍ ቦታ ላይ ኢትዬጲያን የሚያክል ታላቅ ሃገር ወክለው ቆመው የዚህ መሰልየህፃን ስህተት ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል???/እሺ ሳያውቁ ነው የዘቀዘቁት ቢባልስ አጠገባቸው የነበሩት ኢትዬጲያውያን ጋርዶች እና ሚኒስተሮች ይህን ማስተካከል ስለምን ተሳናቸው??? ከዚህ በላይ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ፊት የሃገራችንን ባንዲራ ክብር ማጉደፍ ከወዲት አለን??

ከላይ እንደተመለከታችሁት አንድ ግለሰብ ያረጀ ባንዲራ ስላውለበለበ እና ኢቲ ባቀረበው ድራማ ባንዲራ ተቃጠለ መባሉ ድርጊቱን ሊወክል የሚችለው ፈፃሚውን እንጂ የኢትዬጲያን ህዝበ ሙስሊም አይደለም፡፡ ወንጀለኛውን ተከታትሎ ለፍርድ የማቅረብ ተቀዳሚ የመንግስት ተግባር ነው፡፤

መንግስት ይህን የአገር ክብር የሚያዋርድ ስራ የሰራውን ግለሰብ ለፍርድ አቅርቦ ለሌላው መቀጣጫ ማድረግ ሲገባው ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት በእምነት ቦታዎቻችን ላይ የእምነት መሪዎቻችንን ወይንም መጅሊስ አመራሮችን እንምረጥ፣አህባሽ የተሰኘውን እምነት መንግስት በግዳጅ በሙስሊሙ ላይ አይጫንብን፣ መንግስት በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ አይግባ፣ህገ መንግስቱ ይከበር፣ የእምነት ነፃነት ይከበር ብሎ የጠየቀን ህዝበ ሙስሊም ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር ለማጋጨት አክራሪዎች ሸሪአ መንግስት ነው የጠየቁት፣ባንዲራ እያቃጠሉልህ ነው በማለት በሚሊዬን የሚቆጠረውን የኢትዬጲያ ሙስሊም በሃሰት መወንጀል ምን ይሉታል???

አክራሪነትን የምንዋጋው መንግስት ደስ ስላለው ሳይሆን ሃይማኖታችን ኢስላም ስለማይፈቅድልን ነው!!!

የኢትዬጲያ ህገ መንግስት አክራሪነትን ቢፈቅድ እንኳን እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አክራሪነትን አንደግፍም!!!

የኢትዬጲያ ህገ መንግስት አሸባሪነትን ቢፈቅድ እንኳን እኛ ኢትዬጲያውያን ሙስሊሞች አሸባሪነትን አንቀበልም!!!!

ተቻችሎ እና ተከባብሮ የመኖር ባህላችንን በመንግስት ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ አናደፈርስም!!!

አላሁ አክበር!!

No comments: