Wednesday, August 14, 2013

ሃገራዊ ጥሪ ለወገኞቻችን

ሃገራዊ ጥሪ ለወገኞቻችን

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል
በቤተክህነትና በክርስትና ተቋማት ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ የሚያንገበግባችሁ ወገኖች ሁሉ፤
በየመስጂጁና ተቋማት ላይ እየተፈፀመ ያለው ደባ የሚያንገበግባችሁ ወገኖች ሁሉ፤
ለወያኔዎችና ሸሪኮቻቸው(ጀሌዎች) እድገትና ምቾት ሲባል ከይዞታችሁ የተፈናቀላችሁ ወገኖቻችን ሁሉ፤
በወያኔ ቱጃሮች ሥራችሁ መቀማቱ ሳያንስ፣ ገቢን ሳይሆን ወገንተኛነትን መስፈረት ባደረገ መመዘኛ ከአቅም በላይ የሆነ የወያኔ ግብር፣ ታክስና መዋጮ የተማረራችሁ ነጋዴዎች፤
ማኅበራችሁ በወያኔ ፈርሶ ወይም ተጠልፎ የጋራ ድምፃችሁን የምታሰሙበት፣ ከቀጣሪያችሁ ከወያኔ ጋር ፍትሃዊ የጉልበታችሁን ዋጋ ክፍያ መደራደሪያ ያጣችሁ ላብአደሮች፣ መምህራን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች፤
ምንም አይነት የአካዳሚ ነጻነት በሌለበት ሁኔታ ጥራቱን ያልጠበቀ ትምህርት እንድትከታተሉ የተፈረደባችሁ፣ ትምህርታችሁን ጨርሳችሁ ከየኮሌጁና ከየዩንቨርስቲው ስትመረቁ እጣችሁ ድንጋይ ማንጠፍ የሆነው ወጣት ተማሪዎች
በነጻነት ወጥቶ መግባት፣ ሰርቶ ለመኖር የተሳናችሁ፣ በገዛ ሃገራችሁ ገና በጎልማሳ እድሜችሁ የወላጆቻችሁ ጡረተኞች እንድትሆኑ የተፈረደባችሁ፣ እንደ ወላጆቻችሁ ትዳር መስርታችሁ ልጆች ወልዳችሁ የመሳም እድላችሁ በወያኔ ዘረኛና ዘራፊ ፖሊሲዎች ጨንግፎ የቀረባችሁ፣ አደገኛ በረሃዎችንና ባህሮችን በማቋረጥ ለመሰደድ ልባችሁ እየከጀለ ያለ የሃገራችን ውድ ወጣቶች፤
በአረብ ሃገራት ለባርነት ስራ በወያኔ እየተሸጣችሁ፣ እጣችሁ ተገዶ መደፈር፣ በፈላው ወሃ መቀቀል፣ መደብደብ፣ መዋረድና ከፎቅ ላይ እየተወረሩ ክቡር ህይወትን ማጣት ለሆነው ውድ እህቶች፣
የሕዝብ ድምጽ ይከበር በማለታችሁ፣ ለሃገር አንድነትና ክብር መሰለፍ እንደ ወንጀል ተቆጥሮባችሁ እንደ ባዕድ ጦር የተበተናችሁና የተገፋችሁ
ጥሪው ቀርቧል ከነፃነት ታጋዮች ጎን በመሰለፍ፣ በመሳተፍ የዜግነት ግዴታችንን ወጣ!!
ከዚህ የበለጠ የግፍ አረንቋ ህዝባችንን አናሳየው!!!
ህዝባችንን እንታደግ! 
ህዝባችንን እንታደግ! 
ህዝባችንን እንታደግ!
ዛሬ ነገ ሳትሉ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይላችንን ተቀላቀሉ።
ተባብረን ወያኔን እናስወግድ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!


No comments: