Thursday, August 1, 2013

አሕጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ፍልውሃ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

በነገው አገር አቀፍ ተቃውሞ ሚዲያዎች እንደሚገኙ ተጠቆመ!

ሐሙስ ሐምሌ 25/2005

አሕጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ፍልውሃ እንዲገኙ ተጋብዘዋል!

ነገ ‹‹የዒባዳና የነፃነት ሳምንት›› በሚል መሪ ርእስ የሚካሄደውን አገር አቀፍ ተቃውሞ ለመዘገብ ሚዲያዎች እንደሚገኙ ተጠቆመ፡፡የረመዳን አራተኛ ሳምንትና የመጨረሻ ጁምአ በልዩ ተቃውሞ የሚካሄድበትን ትእይንት ለመዘገብ የአገር ውስጥና የውጪ ሚዲያዎች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ በአይንቱ ልዩ የሆነውና በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች የሚካሄደው ተቃውሞ ከዚህ ቀደምም የሚዲዎችን ትኩረት ሲስብ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን የነገው ተቃውሞም የሚዲያ ባለሞያዎች ቦታው ድረስ ተገኝተው እንደሚዘግቡት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ተቃውሞ መሰረታዊ የቦታ ለውጥ ማድረጉና በመሀል ከተማ የሚደረግ በመሆኑ የሚስበው ትኩረት ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ነገ ፍልውሀ ካባቢ በሚገኘው ተውፊቅ መስጂድ የሚካሄደው ተቃውሞ በዝምታና በምልክት ብቻ የሚገለጽ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝበ ሙስሊም ይገኝበታልም ተብሏል፡፡ ይህንኑ ትእይንት በቦታው ተገኝተው እንዲዘግቡ ለበርካታ አለም አቀፍና የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ግብዣ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ ክፍለ አሕጉራዊ፣ አሕጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የሚከታተሉ ተቋማት ነገ በፍውሃና አካባቢው ተገንተው የሙስሊሙን ሰላማዊነትና ዲሲፕሊን የተሞላበት ተቃውሞ እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል፡፡


No comments: