Thursday, August 1, 2013

የጅንካ ከተማ ወጣቶች ከአንድነት አባላት ጋር በመቀናጀት እየቀሰቀሱ ነው

የጅንካ ከተማ ወጣቶች ከአንድነት አባላት ጋር በመቀናጀት 

እየቀሰቀሱ ነው

የጅንካ ወጣቶች ታሪክ እየሰሩ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በንቃት ለመሳተፍ ከመንቀሳቀሳቸውም በላይ በጅንካና በአካባቢዋ በራሳቸው ተነሳሽነት ቅስቀሳ እያከናወኑ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሞሎካ ውብነህ በ22/11/2005 ዓ.ም በቁጥር 417/107/05 በፃፉት ደብዳቤ ለአንድነት አመራሮች የእንወያይ ጥሪ አድርገው ከ14 የሀገር ሽማግሌዎችና ከጅንካ ከተማ ከንቲባና የተለያዩ የከተማው ባለስልጣናት ጋር በመሆን አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን መሰረዝ አለበት በማለት ለማግባባት ሞክረዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም “ሰላማዊ ሰልፉ አይቀርም መብታችንን አሳልፈን አንሰጣችሁም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የጂንካ ከተማ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) አመራሮችና አባሎች ከኦሞ ሕዝቦች ፓርቲ 1 አባል እንዲሁም ከሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ 1 አንድ አባል የተካተቱበት ኮሚቴ በማዋቀር ሐምሌ 28,2005 ዓ.ም የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ የማስተባበር ስራ  ከሐምሌ 15 ቀን 2005 ዓ.ም አንስቶ መጀመራቸው አይዘነጋም፡፡ #millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=5168#sthash.hnRLfo16.dpuf

No comments: