የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በሞስኮ ኢትዮጵያን በሴቶች ማራቶን የወከሏት አትሌቶች በሙሉ ውድድሩን አለማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ምክንያታቸውን በጽሁፍ እንዲያቀርቡ ለሁለት አትሌቶች ጠየቀ፡፡
በውድድሩ ቲኪ ገላና ና መሰረት ሃይሉ 7 ኪሎ ሜትር ብቻ በመሮጥ በማቋረጣቸው ነው ፌደሬሽኑ ማብራሪያ የጠየቀው፡፡
ቲኪ ገላና በተለያዩ ቦታዎች የማራቶን ውድድር አሸናፊ ስለነበረች በዚህ ውድድር ሜዳሊያ እንደምታገኝ ተጠብቃ ነበር፡፡
የአትሌቲክስ ፌደሬሽኑ ለእነዚህ አትሌቶች በማናጀሮቻቸው ለሚመጡ ውድድሮች ለጊዜው እውቅና እንደማይሰጥም ገልጿል፡፡
ሪፖርተር፡- ዮናስ ተሾመ
No comments:
Post a Comment