የኢህአዴግ ውድቀት
አይቀሬነት
ነው
በሀገራችን ከቀን
ወደ ቀን እያደጉና አየገዘፉ
የመጡትን
የህዝብን
የለውጥ
ጥያቄዎች
ኢህአዴግ
አጥጋቢ
መልስ ሊሰጥ አልቻለም፡፡ እነዚህ
የለውጥ
ጥያቄዎች
መልስ ሊያገኙ ያልቻሉበት ዋንኛ ጉዳይ፣ የሀገሪቱ
ተቋማት
ለህዝቡ
ጥያቄ የሚመጥን መልስ መስጠት የማይችሉ
በመሆናቸው
ነው፡፡
በአጭሩ
የተቋማቱ
ውድቀት
እንደሆነ
ያለምንም
ብዥታ እንረዳለን፡፡
በሃይማኖት ተቋማት
ላይ ተነሱ የሕዝብ ጥያቄዎች
ብንመለከት፡፡
ኢህአዴግ
አገሪቱን
ከተቆጣጠረበት
ጊዜ ጀምሮ እጁን በቀጥታ
በሃይማኖቶች
ውስጥ ማስገባቱን እንረዳለን፡፡ በነጋ በመሸ ቁጥር
ብዙ የሚባልለት ህገ-መንግስት “መንግስት
በሃይማኖት፣
ሃይማኖት
በመንግስት
ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” ቢልም፣
በተግባር
ግን ሕዝብ የሃይማኖት መሪዎቹና
በመንግስት
ካድሬዎች
መካከል
ያለውን
ልዩነት
መለየት
የተቸገረበት
ወቅት ላይ ነው የደረሰው፡፡
የሙስሊሙ
ህብረተሰብ
ላለፉት
ዓመታት
ጠንካራ
የሃይማኖት
ተቋም እንዲኖረው ያለማሰለስ ጠይቋል፡፡ በ1997
ዓ.ም. መደረግ የነበረበትን
የሃይማኖቱ
መሪዎች
ምርጫ እስካሁን ባለመደረጉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ቅሬታውን ሲገልጽ ሰንብቷል፡፡ መጅሊሱ ከኢህአዴግ ተላላኪነት ራሱን አውጥቶ፣ ሕዝበ
ሙስሊሙን
እንዲመራ
ያለመሰልቸት
ጠይቋል፡፡
እነዚህን
የሕዝበ
ሙስሊሙ
ጥያቄዎች፣
መጅሊሱ
መፍትሄ
ሊያበጅለት
አልቻለም፡፡
ሲንከባለሉ የመጡ
ችግሮች
በእንዲህ
እንዳሉ፣
መንግስት
በግልጽ
የአንድ
ሃይማኖት
አስተሳሰብ
በሙስሊሙ
ላይ ለመጫን ተነሳ፡፡ ይህን አስተሳሰብ ለማስረፅ
በተዘጋጁ
ስልጠናዎች
ላይ መንግስት በግልጽ የዚህ አስተሳሰብ ደጋፊነቱን
ማወጁ፣
ብዙዎችን
አስደነገጠ፤
አስቆጣም፡፡
ዘወትር
የሚምልበትን
ሕገ-መንግስት በግላጭ ጣሰ፡፡ ሰልጣኞቹ በካድሬዎች እየተመለመሉ ሥልጠና እንዲወስዱ ዋንኛ ስራ አድርጐት
ቀጠለ፡፡
ይህን ድርጊቱን የተቃወሙ ሙስሊሞችን “አክራሪዎች” የሚል ተለጣፊ ስም
በመስጠት
ልዩነቶችንና
አለመግባባቶችን
ይበልጥ
እንዲሰፉ
አደረገ፡፡
በዚህ መሃል መጅሊሲ የመፍትሄው
አካል መሆን ሲገባው፣ የችግሩ
አካል ሆኖ በግልጽ ወጣ፡፡
የሙስሊሙን ህብረተሰብ
መሠረታዊ
የመብት
ጥያቄዎች
ኢህአዴግ
አጥጋቢ
በሆነ መልኩ ሊቀርፋቸው ሲገባ፤
የህዝበ
ሙስሊሙን
ወኪሎች
እንደለመደው
ለቁጥር
የሚያዳግት
ታፔላ ለጠፈባቸው፤ በህገ-ወጥነት፣ በተላላኪነት፣
በአሸባሪነት፣
በሃይማኖት
ጽንፈኛነት
/አክራሪነት/፣ በፀረ-ሰላምና
ፀረ-አንድነት፣ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካ አጀንዳ
የሚያራምዱ፣
የነውጥ
ኃይል ወደሚል ፍረጃ ገባ፡፡ ሕዝበ
ሙስሊሙ
ግን እጅግ ጨዋነት በተሞላበት፣
ከስሜት
በወጣና
ብዙዎቻችን
ባስደመመ
መልኩ፣
ፍጹም ሰላማዊ
የሆነ ተቃውሞውን
ቀጠለ፡፡
በዚህ ሰላማዊ
እንቅስቃሴ
የተበሳጨው
ኢህአዴግ፣
የጸጥታ
ኃይሎችን ወታደሮችንእና ፌደራል
ፖሊስን በማሰማራት
ሙሰሊሙ
ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ወስዷል በዚህም ጥቂት የማይባሉ ወንድሞቻችን ና ወገኖቻችንን ገድሏል፤ መስጂድ
ሰብሮ በመግባት የተከበሩ የእምነት ተቋማትን ክብር ደፍሯል፡፡ በመጨረሽያም
በህዝበ
ሙሲሊሙ
የተመረጡ
የኮሚቴ
አባለትን
ና ጋዜጠኞችን በጅምላ አስሯል፡፡ በቅርቡ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በታሰሩት የሙስሊም ተወካዮች ላይ የሰባዓዊ መብት
ጥሰት መፈጸሙን ዘግቧል በአፋጣኝ እንዲያቆምም ጠይቋል፡፡ በተለይ የሙስሊሙ
መሪዎች
ላይ ድብደባና ቶርቸር መፈጸሙን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
የሃማኖት ተቋም
ነጻነት
ጥያቄ አንግበው የተነሱ ወገኖችን ላይ የደረሰውን የሰባዓዊ
መብት ገፈፋን አጥብቀን እናወግዛለን፤ በዚህ ተግባር የተሳተፉ
አካላትም
የፈጸሙት
የሰባዓዊ
መብት ጥሰት በኃላፊነት እንደሚያስጠይቃቸው
መገንዘብ
ይኖርባቸዋል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ
የመብት
ጥያቄ በዱላ፣ በጠመንጃና በእስር መፈፀሙ አይፈታም ብለን እናምናለን፡፡ የህዝበ
ሙሰሊሙ
ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው የኔ
የሚለው፣
ሊወክለው
የሚችል፣
ከፖለቲካ
ጣልቃ ገብነት የፀዳ ነጻና ጠንካራ
ተቋም ሲመሰርት ብቻ ነው፡፡
በክርስትና የሃይማኖት
ተቋማት
(በተለይም
በኦርቶዶክስ
ተዋህዶ)
ውስጥ የሚታየው ጉድ፣ ከሙስሊሙ ተቋማ
ከሚታየው
ችግር ከአስር እጥፍ በላይ የገዘፈ
ነው የሚል እምነት አለን፡፡
የቀድሞ
ጠቅላይ
ሚኒስትር
ታምራት
ላይኔ ከእስር ከተፈቱ በኃላ ከአሜሪካ ኤምባሲ
ኃላፊዎች
ጋር ያደረጉትን ወይይት ዊኪሊክስ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ አቶ ታምራት
እንደገለጹት
“የኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን
ፓትሪያሪክ
አቡነ መርቆሪዮስን በእኔ ፊርማ ከቦታቸዉ
እንዲነሱ
አድርጌ፣
ለእኛ ስርዓት ይሰሩልናል ያልነዉን እንዲሾሙ አድርገናል” ብለዋል፡፡
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ሃይማኖት
ውስጥ ተቋማዊ አሰራር ብሎ ነገር የለም፡፡
ሲኖዶሱ
ትርጉም
ያለው አካል መሆን አልቻለም፤
ተሰብስቦ
የሚወስነው
ውሳኔ ተግባራዊ አይሆንም፡፡ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የመንግሰት ከፍተኛ
ባለስጣናት
እየተገኙ
የሚፈልጉትን
ውሳኔ እያስወሰኑ ወንጀል ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ “ለምን?
እንዴት?” በማለት
ጥያቄ ያቀረቡ ጳጳሳት መስቀላቸውን እያስቀመጡ ቤተመንግሥት እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ ዛቻና ማስፈራሪያ
ተፈጽሞባቸዋል፤
በመኖሪያቸው
ውስጥም
የተደበደቡ
አባቶች
አሉ፡፡
መንግሥት ካላጣው
መሬት በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ታላቅ የቅድስና ቦታ
ተደርጎ
የሚቆጠረውን
ዋልድባ
ገዳም በእብሪትና በማን አለብኝነት በልማት
ስም ደፍሯል፡፡ የዋልድባ ገዳም መጋቢና የገዳሙ
ምሰሶ ሆነው በዙሪያው የሚገኙ
ሶስት ቤተክርስቲያናትን አፈራርሶል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ለረጅም ዓመታት
በምንኩስና
የሚኖሩ
አረጋዊያንና
ገዳሙን
የሚያገለግሉ
“አትንኩብን፤
የእምነት
ነፃነታችን
ይከበር”
ብለው ቢጮሁ “ፀረ-ልማት፤
ሽብርተኞች”እያለ አሸማቋቸዋል፡፡
ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ
ስናየው
ሁሉን የመቆጣጠር አቅጣጫ የሚከተል ኃይል ነው፤ ቀጥተኛ
የሆነውን
የሙስሊሞችን
የተቋም
ነጻነት
ጥያቄ እንኳን መፍቀድ የማይፈልግ አምባገነን ነው፡፡ በመሠረቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ዘርፍ
ከሱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ተቋማትን
በሀገራችን
እንዲያብቡ
በፍፁም
አይፈቅድም፡፡
ያለፉት
21 ዓመታት
ሂደቱ በግልጽ የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡
ነጻ ተቋማት
ሊኖሩ የሚችሉት ዴሞክራሲና ነጻነት በተከበረበት ሀገር ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም
ሁላችንም
ለዴሞክራሲያዊ
ስርዓት
ምስረታና
ለሰባዓዊ
መብቶች
መከበር
ለሚደረገ
ትግል የድርሻችንን ልናበረክት ይገባል፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ
ኢትዮጵያ
በክብር ለዘላለም ትኑር!
No comments:
Post a Comment