Friday, August 2, 2013

ድምፃችን ይሰማ ካወጣው መግለጫ ላይ ተቆርጦ የተለጠፈ

ድምፃችን ይሰማ ካወጣው መግለጫ ላይ ተቆርጦ የተለጠፈ



"የዛሬው አብይ ተቃውሞ ይደረግበታል ተብሎ የነበረው የተውፊቅ መስጂድ ትእይንት መሰረዙ የተገለጸ ቢሆንም ይህ 

ያላስደሰተው መንግስት በመስጂዱ ግርግር በመፍጠር የራሱን ለፕሮፖጋንዳ ፍጃታ የሚውል ቀረጻ ሲያካሄድ ነበር፡፡ በፍልውሃ 

ተውፊቅ መስጂድ ለጸሎት የተሰበሰበው ሕዝብ ተለምዷዊ መንፈሳዊ ተግባሩን በመፈጸም ላይ ሳለ የመንግስት ኃይሎት ትንኮሳ 

ያደረጉ ሲሆን ግርግር በመፍጠርም ለዚሁ ወቅት የተዘጋጁ ታጣቂ ፌዴራል ፖሊሶች ሙስሊሙ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ሲያደርጉ 

ተስተውሏል፡፡ በተለይም በሴት እህቶቻችን ላይ የተካሄደው ድብደባ የከፋ እንደነበር ታውቋል፡፡ በጣም በርካታ ሙስሊሞችም 

ከመስጂዱ ተወስደው ታስረዋል፡፡ ይህ ድርጊት በአካባቢው የሚገኙ ሁሉ መንግስት ከዚህ ቀደም በምን መልኩ ኹከት እየፈጠረ 

ሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ የኃይል እርምጃዎች ይወስድ እንደነበር የታዘቡበት አጋጣሚ ነበር፡፡

ይህን ግርግር ለራሳቸው የፖለቲካ ፍጆታ እና የምሽት የኢቴቪ ዜና ለመጠቀም የቋመጡት የመንግስት ጋዜጠኞች ቀረጻ 


በማካሄድ ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ተውኔት ሲያዘጋጁ መዋላቸውም ተረጋግጧል፡፡ ለዚህ አላማ የተዘጋጁ ግለሰቦችንም የሙስሊም 

ኮፍያ በማልበስ ተገቢ ያልሆኑ ንግግሮችን እንዲናገሩ እና ድረጊቶችን እንዲፈጽሙ በማድረግ ቀረጻ ሲያካሄዱባቸው 

እንደነበርም እማኞች አስረግጠው gelልጸዋል፡፡ ተመሳሳይ ቀረጻ በአንዋርና ኑር መስጂዶች ላይ ተካሄዷል፡፡ በዛሬው ምሽትም 

መንግስት ‹‹አክራሪዎች ኹከት ሊቀሰቅሱ ሲሉ እርምጃ ተወሰደባቸው፤ በቁጥጥር ስር ዋሉ›› የሚሉና መሰል የፕሮፖጋንዳ 

ዘገባዎችን በኢቴቪና በሌሎች ብዙሀን መገናኛዎች እንደሚያሰራጭ ይጠበቃል፡፡ ይህም የመንግስትን ተስፋ እየቆረጠ መሄድና 

የትግላችን አይሎ መሄድና መንግስትን መፈናፈኛ እንዳሳጣው አመላካች ነው"

No comments: