በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና ካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ እና ካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ግብረ አበር መምህራኖች በኮሚኒትው ንብረት ላይ የሚፈጽሙትን ዘረፋ አወገዙ ።
በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ገንዘብ የላኣግባብ በልጽገዋል የሚባሉ በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት ረዕ ስ መምህር አቡል ባሴጥ፡ጀማል እና አንዳንድ ዲፕሎማቶች በህዝብ ንብረት ላይ ለፈጸሙት ዘረፋ መንግስት በህግ እንዲጠይቅላቸው ትላንት አርብ ኦገስት 16 2013 ምሸት ህዝበ ነዋሪው ባደረገው ስብሰባ ገለፀ።
አንዳንድ ወገኖች እንደሚገልጹት እንዘህ በኢትዮጵያ የሪያድ ዲፕሎማቶች እና የነሱ ተላላኪ የሆኑ አንዳንድ መምህራ በኮሚኒቲው ት/ቤት ላይ ላለፉት አራት አመታት የፈጸሙት ዘረፋ በውል እንደማይታወቅ በማብራራት በአሁኑ ሰአት የሳውዲ መንግስት ያወጣውን አዋጅ በመተራስ ት/ቤቱን እስከነ አካቴው በመዝጋት ከተጠያቂነት ለማምለጥ፡እየተራወጡ መሁኑን በአጽኖት ይገልጣሉ።
በአጭር ግዜውስጥ በሃብት የተበሸበሹት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና የዲፕሎማቱ ጀሌ መምህራኖች የት/ቤቱ ካዝና ላለፉት 4 አመታት ኦዲት እንዳይደረግበት እንቅፋቶችን በመፍጠር በኮሚኒትው ንብረት ኢትዮጵያ ውስጥ፡ ህንጻ ያላሳነፀ አሊያም እዚህ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በሚያስደንቅ ሁኔታ የአዳድሲ ሞዴል ላንድክሮዘሮች ባለቤት ያልሆነ የነሱ ተላላኪ መምህር እና ወሬ አእቀባይ እንደሌለ ንምጮች ይናገራሉ ።
እነዚህ ምንጮች በማያያዝ ዘንድሮ በነዚህ ዲፕሎማቶች ከገባበት አዝቅ መውጣት የተሳነው የሪያድ አለም አቀፍ የህዝብ ት/ቤቱ ከመዘጋቱ እና በቀረው የት/ቤቱ ሃብት እና ንብረት ላይ የለየለት ዘረፋ በገሃድ ከመፈጸሙ በፊት መንግስት በፌደራሉ ፀረ ሙስና እና ስነ ምግባር ኮሚሽን መ/ቤት እየትጋዘ ሃገር ውስጥ፡ እያከሄደ እንዳለው ቁጥጥር እዚህ ሳውዲ አረቢያ በሚገኙ መንግስትን ወክለው የተሰማሩ ዲፕሎማቶች በኮሚኒቲው ንብረት ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘረፋ ግዜ ሳይሰጥ፡ማስቆም እና የት/ቤቱን ካዝና ታውቂ በሆኑ የሂሳብ ሰራተኞች አስመርምሮ ወንጀለኞችን በስቸኳይ ለፍርድ ማቀረብ እንደሚገባው ተሰብሳቢው ጨምሮ ገልጾል። ይህ በዚህ እንዳለ እንዚህ ዲፕሎማት እና መምህራኖች ት/ቤቱን ለመዝጋት ያላቸውን ህልም በማጠናከር ሰሞኑንን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት እድሳቶቸችውን ፎርማሊቲ አሞልተው ወደ ትቤቱ ልጆቸቸውን ለማስመዝገባ የሚመጡ ወላጆችን በተለያዩ ምክንያቶች እንዳይመዘገቡ በማገድ ላይ መሆናቸውን ዘግይቶ የደረሰን መረጃ ይገልጻል ።
ይህ ስብሰባ በሚቀጥለው ስምንት ኦገስት 23 2013 አርብ በኢትዮጵያ ሰአት አቋጣጠር ከምሽቱ 3 00 ጀምሮ በሪያድ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡እንደሚካሄድ ይጠበቃል።እንደሚታወቀው በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በህዝብ ላይ በፈጸሙት ተደጋጋሚ ጥፋት በሳዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሀመድ ሃሰን ለግምገማ በመንግስት አስቸኮይ ተእዛዝ ሀገር ከርመው ወደ ነበሩበት ሃገር ሳውዲ ቢመለሱም መንግስት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ሰሞኑንን ወድ ሃገር ጠቅልለው እንደሚገቡ ይጠበቃል።
ምንጮጭች ለአብነት የላኩልንን ረእሰ ምመህሩ በአጭር ግዜ ውስጥ ካፈራቸው ንብረቶቹ ጥቂቱን ከዚህ በታች ይመልከቱ !! ሙሉ ዝርዝሩን በሰሞኑ ተከታታይ ሰፊ ዘገባ ይጠብቁ
ከ Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
No comments:
Post a Comment