Saturday, August 17, 2013

ተመጣጣኝ እርምጃ

በአገራችን ተመጣጣኝ እርምጃ ማለት ከመግደል ያላነሠ ከመግደል ያልበለጠ እርምጃ 

ማለት ነው::ምንም ይሁን ምን ተቃውሞን በጩኸት ለገለፀ በጠመንጃ መስጠት 

ተመጣጣኝ ሆኖ አያውቅም: ለነገሩ የቴሌቭጅን ቇንቇና የአማርኛ ቇንቇ ለየቅል 

ነው:: ቴሌቭጅን "ሠማያዊ ፓርቲ በአንድ ከተማ የተቃውሞ ሠልፍ አካሔደ" 

ካለ የአማርኛ ትርጉሙ "መንግስት በቀጣዩ ሳምንት በአንድሺ ከተሞች 

ሠማያዊ ፓርቲ አይወክለንም" የሚል ሠልፍ ያስደርጋል ማለት 

ነው::ቴሌቭጅን "የቀድሞ ሜሶፖታሚያ ነዋሪዎች መንግስት በአክራሪዎች 

ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ::" ካለ የአማርኛ ትርጉሙ "በቀጣይ 

ጁምዓ ወገራ አለ::" ማለት ነው:: ቴሌቭጅን ያችን ባንዲራ እያሳየ "ፀረ ሠላም 

ሀይሎች ለባንዲራ ያሳዩት ንቀት አሳፋሪ ነው ሲሉ የኢቲቪ ዜና አንባቢዎች ገለፁ::" 

ካለ የአማርኛ ትርጉሙ "ያቺን ባንዲራ እዛ ቦታ ያመጣት የአንባቢዎች ዘመድ 

ነው ማለት ነው":: 

(ከadis guday መፅሔት በሀብታሙ ስዩም ከተፃፈው የተወሠደ)

No comments: