"ፍኖተ ኢህአዴግ"
በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ02 ሳቢያን ሠፈር ልዩ ስሙ ጐሮ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ኗሪ የነበረውና መንግስት/የድሬደዋ አስተዳደር "ለልማት" በሚል ለወሰደበት መሬትና ላፈረሰበት ቤት ምትክ አልሰጠኝም በሚል ላደረገው ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ያላገኘው ጌታሁን የተባለ ወጣት በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ነገሩ እንዲህ ነው
ይህ ጌታሁን የተባለው ወጣትና ወንድሙ የመስተዳድሩ ባለሥልጣኖች ባዘዙት መሠረት መሬታቸው ተወስዶ ቤታቸውም ይፈርስባቸዋል::ከረጅም ሙግትና ጊዜ በሗላም ጌታሁን ተተኪ መሬቱን ያገኛል
ቀጥሎ እነዚህ ወንድማማቾች የቀረውን የጌታሁን ወንድም መሬት መጠየቃቸውን ይቀጥላሉ በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ::ሆኖም መልስ ሊያገኙ አልቻሉም: ጌታሁንም ወንድሙን ወደ ሥራው ሸኝቶ ብቻውን ጉዳዩን መከታተል ይጀምራል እጅግ በሚገርም ሁኔታ "የወሰዳችሁት አይበቃችሁም ወይ?"መባል ጀመረ
አብዝቶ ጠየቀ ጌታሁን "የወንድሜን ቦታ"ብሎ መልስ አጣ እጅግ ደጋግሞ ጠየቀ የሠማው የለም::
በመጨረሻም ይህ ጌታሁን የተባለ በምግባሩ ተወዳጅ የነበረና በሥራውም በመንግስት ት/ቤት ውስጥ መምህር የነበረ ወጣት መረር ያለ ውሳ ወሰነ
ሰውነቱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን ይለኩሳል::በመንደድ ላይ ሳለ ሰዎች ይደርሱና ተረባርበው እሳቱን ያጠፉለትና ወደ ሆስፒታል ይወስዱታል
ድል ጮራ ተብሎ በሚታወቅ የመንግስት ሆስፒታል ለአራት ቀናት ሲረዳ ቆይቶ በትናንተው ዕለት ሞቷል::
የሚገርም ዜና!
"ለልማት"በሚል በተወረሰውና ቤቶች በፈረሱበት ቦታ ላይ ከ2ዓመት በላይ ምንም የተሠራበት ነገር አለመኖሩን አረጋግጫለሁ
በጣም የሚገርም ዜና!
የተቃጠለውን የጌታሁንን አስከሬን ከሆስፒታሉ የወሰዱት የፌዴራል ፖሊሶች ናቸው
እጅግ በጣም የሚገርም ዜና!
ማንም ባለሥልጣን/ የመንግስት አካል ያሉት ነገር የለም

No comments:
Post a Comment