Saturday, August 3, 2013

ጥብቅ ማሳሰቢያ ከድምፃችን ይሰማ

ጥብቅ ማሳሰቢያ ከድምፃችን ይሰማ

ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሰላሙን እንዲያስጠብቅ መልእክት ተላልፏል! በብዙ የአገሪቱ አካባቢዎች መረጋጋት
እንዳይሰፍን መንግስት እየሰራ ይገኛል፡፡ የሙስሊሙ ሰላማዊነት እንቅልፍ የነሳው መንግስት ሁኔታዎች ወደ አለመግባባት እና ግጭት እንዲያመሩ እየሰራ ነው፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ መንግስት ሊፈጥር እያሰበ ያለውን ኹከት በመገንዘብና ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በማሰብ የመንግስትን ትንኮሳ ቸል እንዲልና በትእግስት እንዲያሳልፍ አስቸኳይ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡

የመንግስት ቀዳሚው ፍላጎት መጀመሪያ እንደታየውም ኹከትና ግጭት በመፍጠርና ጥፋት በማድረስ፣ ሙስሊሙን ኅብረተሰብ ለመወንጀልና ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም በመሆኑና ይህም በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ በመሆኑ፤ መንግስት ኹከት ሲቀሰቅስ በቸልታና አይቶ በማሳለፍ በመንግስት ወጥመድ ላለመውደቅ ሁሉም ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

ከምንም በላይ ሰላማዊነታችን ዋጋ የምንሰጠው መሆኑን ሁላችንም ከግንዛቤ በመክት ሰላማችንን ሊነጥቁ የሚመጡ ኃይሎን በሰላም ብቻ እነድንመልሳቸው አደራ እንላለን፡፡

አላሁ አክበር!

ላልሰሙት በማሰማት ሃላፊነታችንን
አንወጣ!!!


No comments: