Friday, August 2, 2013

ይህ የተገፋ ህዝብ እንዳጎነበሰ አይኖርም ቀና ያለ እለት ወዮላቹ!!!

ባልታጠቀ ዜጋ ላይ እየተፈጸመ ያለ መንግስታዊ ሽብርተኝነት

ይህ የተገፋ ህዝብ እንዳጎነበሰ አይኖርም ቀና ያለ እለት ወዮላቹ!!!

አንድነት ያልተመዘገበ ሀገወጥ እና አሸባሪ ከሆነ የተወነጀለበት ተቀባይነት ያለው ክራይቴሪያ ይነገረን እና እናውግዘው::ሙስሊም ወገኖቻችንም ጥያቄያቸው ግልጽ እና ግልጽ ነው ካልሆነ የሚዋከቡበት ምክንያት የለም ካለ ይነገረን እና እናውግዝ ተደጋጋሚ ጸሎት አንፈልግም መንግስታዊ አሸባሪነትን እያወገዝን ወያኔን በትእግስት እየጠበቅናት ነው ይህ ያበጠ ነገር የፈነዳ እለት ወዮላቹ...የምትገቡበት አታገኙም:: እንደ ደርግ ባለስልጣናት ወህኒ አንወሽቃችሁም:: ወህኒ እኮ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም::
በዛሬው እለት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ በቅጥር ፖሊሶች ሲፈጸም የዋለው ወከባ የወያኔ ጁንታ በጫካ ቆይታው የለመደውን ማፍያዊ ምግባሩን ያንጸባረቀበት እና ያስመሰከረበት ነው:; ባዶ እጁን ሙስላያ ይዞ ወደ መስኪድ የሚተመስን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ማዋከብ እና ማሰር ማፈስ ከሽብር ተለይቶ አይታይም:: ይህ የሕወሓት ደባ የያዘችውን ወታደር እና መሳሪያ ተማምና መንግስታዊ ሽብር በዜጎች ላይ ፈጥራለች:: ይህንን መንግስታዊ ሽብር እያንዳንዳችን ልናወግዘው ይገባል::

የአንድነት ፓርቲ እያደረገ ያለውን የሚሊዮን ድምጾች ለነጻነት ዘመቻ ተከትሎ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች ህግ የለም ወይ እስኪያስብል ድረስ ወከባ እና እስር በመንግስታዊው አሸባሪዎች እየተፈጸመ ነው:: ከመቀሌ አንስቶ እስከ ወላይታ ሶዶ ድረስ ሰዎች በሃገራቸው ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው እና ህዝባዊ የጥያቄ ድምጾችን እንዳያሰሙ ማድረግ ወያኔ በስልጣን ላይ የመቆየት ህልሙን በገሃድ እያሳየ ነው::

ለይስሙላ በወረቀት የታተመው የሃገሪቱ የበላይ ህግ ተብየው ህገ መንግስት በየት ቦታ በየትኛው አገር በየትጫው ቀን እና ሰአት በእነማ እየተተረጎመ እንደሆን ግልጽ ሊሆንልን አልቻለም እንደዜጋ የሃገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለን እስከተነሳን ድረስ አቤቱታችን ሊታይ ይገባዋል:: አሸባሪ ይውሆኑ ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል::

በወላይታ ሶዶ አፈናው እና እስሩ ሰፋ ባለ መልኩ መቀጠሉ እና በባህር ዳር የቅስቀሳ ሰዎችን ለማዋከብ መፍጋቱ እንዲሁም በመቀሌ በ24 ሰአት ለቀህ ውጣ የተሰኛው ቀጭን ትእዛዝ ትግራይ ኢትዮጵያ አይደለችም ወይ? አስብሏል:: ይህም ይባስ ተብሎ ህገመንግስታዊ መብቶችን የተጠቀሙ ግለሰቦች ካለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወደ እስር ቤት መወርወር የት ነን ያለነው ወዴትስ እያመራን ነው የሚል ጥያቄዎች ደጋግመን እንድናነሳ አስገድዶናል:: ችግር ካለ ይነገረን እና አስፈላጊውን እርምጃ መንግስት ቢወስድ እንስማማለን አንድነቶች ግን ወረቀት ይዘው ነው ለነጻነት የዘመቱት ይህም የሚያሳድድ የሚያዋክብ ከሆነ በህገመንግስቱ ውስጥ ይካተት እና የነጻነት ጥያቄው ይቆማል::

የህዝቦች ጥያቄ ማለት ለወያኔ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚተረጎም አልተረዳንም ስልጣንን ለማራዘም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የባለስልጣናት እርስ በእርስ አለመነባበብ የሚያስከትሉት ግድፈቶች በሃገር እና በህዝብ ላይ ከፍተጫ ጥፋት ያስከትላሉ:: በወከባ እና በእስር ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም:: የማይነጋ መስሏት.......እንዳይሆን ነገን ለሃገር እና ለህዝብ እናስብ...ድንጋይ እየቆለሉ ይኸው ፎቅ ሰራንልህ.. በብድር እየተከናነቡ መንገድ አሰራንልህ .... ወዘተ ቢባል ይህ ህዝብ ቅድሚያ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ነጻነት ይፈልጋል እና በጥሞና እና በአትኩሮት ሊታይለት ይገባል:: 

No comments: