መለስ ዜናዊ ባይሞቱ ሥልጣን ይለቁ ነበር?
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቤተ መንግሥት እንደገቡ ከገቧቸው
ቃልኪዳናት መካከል ‹ሥልጣን ላይ አለመክረም› አንዱ ነበር፡፡ ግንቦት 1983
የቤተመንግሥቱን ደጃፍ ስትጠብቅ ያገኛትን ታጋይ ቃለመጠይቅ ያቀረበላት ጋዜጠኛ
ያገኘው መልስ ‹‹ይህ ቤት ከዚህ በፊት የመንግሥቱ እንደነበረው የመለስ አይሆንም
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ›› የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ገና በማለዳ ትልቁ የሽግግር
መንግሥቱ ባለሥልጣን የነበሩት ፕሬዚደንት መለስ ሕገ መንግሥቱ ሲፀድቅ እና
ዋነኛው ሥልጣን (ሥለጣኑና ጊዜው ገደብ ለሌለው) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲተላለፍ
ፕሬዘንዳንቱ መለስ የአዲሱ አስተዳደር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡ የዚያ
በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸውን የተነጠቁት ታምራት ላይኔ በብስጭት
ዓይናቸውን ሲያጉረጠርጡ የሚያሳየውን ቪዲዮ ከኢቴቪ ገዝቶ መመልከት
ይቻላል፡፡
በዚህ የተጀመረው የሥልጣን ጉዞ መለስን እስከ ዕለተ ሞታቸው ተከትሏቸዋል፡፡
ሊቀናቀኗቸው የሚችሉትን በሙሉ ስም ሲያጠፉ እና ሲያባርሩ መክረማቸውን
የሚክድ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተወዳጅነትን
ለማትረፍ የበቁትን ብቸኛውን የሕወኀት አባል - አርከበ ዕቁባይን - በግልጽ
ጠምደዋቸው ነበር፡፡ አርከበ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ማድረጋቸውን ለመቀስቀሻነት
ለመጠቀም በአደባባይ ቢልቦርድ ላይ መሰቀሉን አስመልክተው ሲያሾሙሩ ‹‹እኛም
ማስታወቂያ አልሰቀልንም እንጂ ተመርምረናል›› ዓይነት የመንደር ትችት
ሰንዝረዋል፤ የኋላ ኋላም አርከበን ለሕዝብ ወደማይታዩበት ኃላፊነት በመሾም
አባርረዋቸዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2008 የወጣ የዊኪሊክስ መረጃ እንደሚያመለክተው በሕወኀት ጉባኤ
ላይ እኚሁ መለስ ያልወደዷቸው አርከበ ሊቀመንበር እንዲሆኑ ቢመረጡም
‹‹በአርከበ እምቢተኝነት›› መለስ በሊቀመንበርነታቸው ቀጥለዋል ይለናል፡፡ እዚህጋ
አርከበ እውን ‹‹እምቢ›› ብለዋል? ለምን? የሚሉትን ጥያቄዎች እንተውና ሌሎች
መረጃዎችን እናንሳ፡፡
አቶ መለስ ምርጫ 1997 ከመካሄዱ በፊት ሥልጣን እንደሚለቁ ሲናገሩ ነበር፤
አልለቀቁም፡፡ በምርጫ 2002ም ሥልጣናቸውን እንደሚያስረክቡ ተናግረው የነበረ
ቢሆንም፣ ‹በመተካካት አስፈፃሚነት› ስም አራዘሙት፡፡ በሥልጣን ማራዘሙ ወቅት
መለስ የሚነግሩን ‹‹በእርሳቸው ፍላጎት ሳይሆን በፓርቲያቸው ትዕዛዝ
ሥልጣናቸውን እንደቀጠሉ›› ነበር፤ ‹እባክህ ቆይልን› የሚሉት ተማፅኖዎች (ለኔ
ድራማዎች) ከመሞታቸው በፊትም፣ ከምርጫ 2002 በኋላ ቀጥለው ነበር፡፡
ስለዚህ መለስ ባይሞቱ ኖሮ በሥልጣን የሚቀጥሉ ይመስለኛል፡፡ በመሞታቸው
ከምቆጭባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ‹የድራማውን መጨረሻ አለማየታችን›
ነው፡፡

No comments:
Post a Comment