..... ህወሓትም እንደ ደርግ! .....!
ትናንት የፌደራል ፖሊስ በሙስሊም
ሰልፈኞች እርምጃ እንደሚወስድ
ሲያሳውቅ መልእክቱ የደርግን ስርዓት
አስታወሰኝ።
የህዝብ ድምፅ በሃይል መጨፍለቅ
እንደማይቻል ህወሓት ከደርግ ተግባር
ትምህርት መቅሰም ነበረበት። ደርግ
ሙሉ ወታደራዊ ዓቅም ነበረው። ወታደራዊ ዓቅሙ ተጠቅሞ የትግራይ
ገበሬዎች የነፃነት ጥያቄ ለመጨፍለቅ
ተነሳ። የትግራይ ሰዎችም የመንግስት
ወታደራዊ ዓቅም ትርጉም እንደሌለው አሳዩን። ህወሓት ይህን ታሪካዊ ትምህርት ማስታወስ እንዴት አቃተው?
በቃ ህወሓትም እንደ ደርግ ሃይል
መጠቀም ነው ወይ መዛት ነው።
ይሄማ የደርግ እስትራተጂ እኮ ነው።
ህወሓት ከደርግ ስርዓት አንዳንድ
ፖለቲካዊ አቅጣጫዎች እየኮረጀ ነው።
ትምህርት መውሰድ ሲገባው መኮረጅ
ምን አመጣው?
ማርያምን! ህወሓት የደርግ ስርዓት
ናፋቂ ነው።
የደርግ ዕጣ እንዳይደርሰው ብቻ።
ደርግን የተከተለ ደርግ የገባበት ይገባል።
ወይ መመሳሰል!?
ትናንት የፌደራል ፖሊስ በሙስሊም
ሰልፈኞች እርምጃ እንደሚወስድ
ሲያሳውቅ መልእክቱ የደርግን ስርዓት
አስታወሰኝ።
የህዝብ ድምፅ በሃይል መጨፍለቅ
እንደማይቻል ህወሓት ከደርግ ተግባር
ትምህርት መቅሰም ነበረበት። ደርግ
ሙሉ ወታደራዊ ዓቅም ነበረው። ወታደራዊ ዓቅሙ ተጠቅሞ የትግራይ
ገበሬዎች የነፃነት ጥያቄ ለመጨፍለቅ
ተነሳ። የትግራይ ሰዎችም የመንግስት
ወታደራዊ ዓቅም ትርጉም እንደሌለው አሳዩን። ህወሓት ይህን ታሪካዊ ትምህርት ማስታወስ እንዴት አቃተው?
በቃ ህወሓትም እንደ ደርግ ሃይል
መጠቀም ነው ወይ መዛት ነው።
ይሄማ የደርግ እስትራተጂ እኮ ነው።
ህወሓት ከደርግ ስርዓት አንዳንድ
ፖለቲካዊ አቅጣጫዎች እየኮረጀ ነው።
ትምህርት መውሰድ ሲገባው መኮረጅ
ምን አመጣው?
ማርያምን! ህወሓት የደርግ ስርዓት
ናፋቂ ነው።
የደርግ ዕጣ እንዳይደርሰው ብቻ።
ደርግን የተከተለ ደርግ የገባበት ይገባል።
ወይ መመሳሰል!?
No comments:
Post a Comment