Monday, August 12, 2013

መንግስት በዶዶላ ሙስሊሙን ለመከፋፈል ያደረገው ሴራ በድጋሚ ከሸፈ፡፡

መንግስት በዶዶላ ሙስሊሙን ለመከፋፈል ያደረገው ሴራ በድጋሚ ከሸፈ፡፡

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ከድርና የአሮሚያ ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ የሆነው አቶ ዳኛቸውና ሌሎችየወረዳው ባለስልጣናት የተገኙበት ስብሰባ በዶዶላ ከተማ ትላንት እሁድ ዕለት መካሄዱ ተሰማ፡፡
የስብሰባው አጀንዳ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በሚል ርዕስ ሲሆን ከኦሮሚያ የመጣው የኦሮሚያ የፀጥታ ባለስልጣን አቶ ዳኛቸው ባደረገው የመክፈቻ ንግግር ላይ በአሁኑ ጊዜ አገራችንን ከፍተኛ የሆነ የአክራሪነትና ፅንፈኝነት በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ተከስቷል በአካባቢው በእስልምና ስም የሚንቀሳቀሱ የአልቃይዳ ፣ የአልሸባብ እና የኦነግ አካላት አገሪቷን ስጋት ላይ ጥለዋታል፤ ለዚሀም ባለፈው አመት በአሳሳ ፣ ከሰሞኑ ደግሞ በኮፈሌ እና በሌሎችም ቦታዎች ላይ በእምነት ሽፋን ችግር መፍጠራቸውና የዜጎችን ህይወት መቀጠፋቸው ይታወቃል ፡፡ስለዚህ በዜጎች መሀል የመቻቻል ባህል ስጋት ላይ ወድቋል፡፡ በአካባቢው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ስላለ ይህን ችግር ከወዲሁ ካልተዋጋን ለወደፊት የማንወጣበት ሁኔታ ስለሚከሰት በዚህ ዙሪያ ከህዝቡ ጋር አንድ አቋም ላይ መደረስ አለበት በማለት የመክፈቻ ንግግሩን አጠናቋል፡፤
የዞኑ ባለስልጣን የሆነው አቶ ሙስጠፋ ከድር ቀበል በማድረግ በአካባቢው የፀጥታው ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ላይ ወድቋል በጋራ መዋጋት አለብን በእስልምና ሽፋን በየመስጊዱ የተሰገሰጉሼኮች እና ኢማሞችን ህዝቡ አውቆ አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል በማለትዕድሉን ለህዝቡ በመስጠት በዚህ ላይ ምን ትላላቹ በማለት ከተሰብሳቢው አስተያየት ጠይቀዋል፡፡
ራሱ መንግስት በጅምላ ለጨፈጨፈው ሰላማዊ ህዝበ ሙስሊም በአካባቢው ሼኮችና ኡለሞች ላይ ለማላከክ የፈለጉ መሆኑን የገባቸው የዶዶላ ህዝብ ወደ ራሳቸው መልሰውባቸዋል፡፡
አስተያየት ሰጪዎች በመነሳት ምንድን ነው እያላቸሁ ያላችሁት እናንተ የሰራችሁትን ወንጀል ወደ ሼኮቹና ህዝቡ ማላከክ ፈልጋችሁ ነው ይህ እንኳን አይሳካላችሁም፡፤ ህዝቡ ነቅቶባችኋል ህዝብን እያሸበረ ያለው መንግስት ነው፡፤ የህዝቡን ሰላም የነሳው መንግስት ነው፡፡ የህዝብ የፀጥታ ስጋት የሆነው መንግስት ነው፡ ለምን ትዋሻላችሁ የኮፈሌ ህዝበ ሙስሊም ምን አድርጎ ነው የጨፈጨፋችሁት ነገ ከመጠየቅ አትድኑም፡፡ ይሀ ሁሉ ጦር እዚህ ማስፈር ለምን አስፈለገ ፡፡ሙስሊሙ የጠየቀው ህገ መንግስቱ ይከበር በእምነታችን ጣልቃአትግቡብኝ አህባሽን በግድ አትጫኑብኝ የመረጥኩትን ኮሚቴ ፍቱልኝ ነው እንዲ ብሎ መብቱን መጠየቅ አሸባሪነት ነው እንደውለስሙ ህገ መንግስቱ የበላይ ነው ትላላችሁ ነገር ግን በወረቀትብቻ ነው ያለው፡፤ ዲሞክራሲ አለ ትላላችሁ እንከዋን ዲሞክራሲ ሽታውም የለም፡ ህዝብን እያሸበራችሁ አሸባሪ ያሰጋናል ትላላችሁ፡፤ እኛ ባሁኑ ሰዓት ትልቅ የሽብር ስጋት የፈጠረብን የህዝብን ድምፅ መስማት የተሳነው መንግስት ነው፡፤ የራሳችሁንባህሪ ወደ ህዝቡ ማላከክ ይቅርባችሁ በማለት ከህዝቡ ያልጠበቁትን ምላሽ ተሰቷቸዋል፡፡
በተጨማሪም ሌላ አንድ ሽማግሌ ኢማሙን ለምን አሳልፋቹ ለምን አትሰጡም ለተባሉት መልስ ሲሰጡ ሙስሊሙ አንድ አካል መሆኑን አታቁም እንዴት እንደዚህ ትላላችሁ ይሄ የማይታሰብ ነው፡፡ ችግርና ሁከት እየፈጠራችሁ ያላችሁት እናንተው ስለሆናችሁ ራሳችሁ መፍትሄ ፈልጉ ህዝበ ሙስሊሙ እንደሆነ ሰላም ነው በማለት ቁርጥ ያለ መልስ ለመንግስት አካላት መልስ ሰጥተዋል፡፡
እጅግ በጣም የሚገርም እና ያልተጠበቀ ንግግር ከዞኑ አስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ከድር የተሰማ ሲሆን ያለፈው አመት አሳሳ ላይ የተከሰተው የደም መፋሰስ ለደዶላ የታቀደ ነበር ፡፤አሁንም ከሰሞኑ ኮፈሌ ላይ የተከሰተው ክስተት ለዶዶላ ህዝበ ሙስሊም የወጣ ፕሮግራም ነበር በማለት በዶዶላ ህዝብ ላይሲያሴር የነበረውን ሴራ በህዝቡ ያልተጠበቀ መልስ የተዳነገጠውየዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ከድር በመደናበር በግላጭ ተናግሯል፡፡
ከህዝቡ አንዱ ሽማግሌ በመነሳት ምንው የዶዶላ ህዝብ ጠላትህ ነው እንዴ በማለት ከጠየቁት በኋላ ይህ ንግግርህ በምዕራብ አርሲ ዞን ለፈሰሰው ደም ሁሉ ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሆንክበህዝብ ፊት በራስህ ላይ ስለመሰከርክ አናመሰግንሃልን በማለትመልስ ሰጥተዋል፡፡ አህባሽ የለም ትላላችሁ እናንተ እዚህ መድረክ ላይ የተቀመጣችሁት ባጠቃላይ አህባሽ ናችሁ ለዚህ አይደል እንዴ ህዝቡ ላይ በግድ መጫን የምትፈልጉት በማለት በቁጣ አሳውቀዋል፡፡
በመጨረሻም ሙስሊሙ የጠየቃቸው ህገ መንግስታዊ የሆኑ የመብት ጥያቄዎችና ኮሚቴው ሳይፈታ ከናንተ ጋር የሚደረግ ድርድር አይኖርም በማለት ህዝቡ ግልጽ አቋሙን አስቀምጧል፡፡
በስብሰባው ያልተጠበቀ ውጤት የተደናገጡት ባለስልጣናት ስብሰባውን ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡
አላሁ አክበር !!!

No comments: