Wednesday, August 14, 2013

12 የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

12 የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ


ነሃሴ (ሰባት)ቀን ፳፻፭ / ኢሳት
ዜና :-የኢድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አስራ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ፡፡
አራት የአሜሪካ፣ ሁለት የሲዊዲን፣ አንድ የአውስትራሊያና አምስት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያኑ ከትላንትናው እለት ጀምሮ በማዕከላዊ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ውለው በነበረበት ወቅት እየተካሄደው ያለው የሙስሊዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከውጭ ሀይሎች ድጋፍ እየተደረገለት እንደሚገኝ ለማስመሰልበመርማሪዎች የተሳሳተ መረጃ እንዲሰጡ ጫና እየተደረገባቸው እንደነበር ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡ በኢዲስ አበባ በኢድ አልፈጥር በዓል ወቅት ቁጥራቸው2ሺህ የሚጠጋ የሙስሊም ተቃውሞ ሰልፈኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተለያዩ አካላት የገለጹ ሲሆኑ ፌደራል ፖሊስ ምን ያህል ሰው በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ከመግለጽ ተቆጥቦ የተያዙት ሰዎች ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለ ማርያም ደሳለኝ እየተካሄደ ያለው የሙስሊሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴየሸርያን መንግስት ለመመስረትያለመ እንቅስቃሴ በማለት የውጭ ሀይሎች እጅ እንዳለበት በመናገር ለማስተባበል መሞከራቸውን የሙስሊሙ ማህበረሰብከእኛ ጥያቄ ውጭየሆነ ንግግር ነው በማለት በመቃወም ላይ ይገኛሉ፡፡

No comments: