Friday, August 2, 2013
ኢቲዮ ሙስሊም 1 - ወያኔ 0
የጥቂት አክራሪዎችን” ሰላማዊ ተቃውሞ ለማክሸፍ መላ ሃገሪቱ ስትታመስ አድራ ስትታመስ ዋለች፤ ሃገሪቱን በመምራት ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ ሰላማዊ ሙስሊም ኢትዮጵያውንን ለመጨፍጨፍ ያዘጋጅው የአመጽ ድግስ በሙሰሊሙ ታጋሽነት ና በአላህ እርዳታ ሊከሽፍ ችሉኣል፡፡ በአንድ ጎሳ ሰዎች በሚመራው ኢቲቪ የተጀመረው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ቀኑን ውሎ ሌቱን አድሮበታል አላማውም በዛሬው ቀን ለታቀደው ጭፍጨፋ ሽፋን መስጠት ነበር፤ በሌላ በኩል በወያኔ ተላላኪ ውሾች ይደረግ የነበረው የቤት ለቤት ቅስቀሳ እስከ ምሽቱ 5 ሰአት ድረስ የዘለቀ ሲሆን መልክቱም ተሃጁድ አትስገዱ የጁምአን ሰላት ባካባቢያቹ መስጂዶች ስገዱ የሚል ነበር፡ የስልጣን እድሜውን ማራዘም እንጂ የዜጎቹ ደህንነት የማያሳስበው ይህ በሙስና የነቀዘ አገዛዝ የ97ቱን እልቂት ለመድገም ቢቁአምጥም የተመኘውን ሳያገኝ ቀርቱኣል፡፡ ጥቂቶች በሚል አባዜ የተጠመዱት እነዚሁ የአጼ ዩሃንስ የልጅ ልጆች በስልጣን ዘመናችውም ሆነ በትግል ግዚያችው ከገጠማቸው ፈተና ትልቁና ከባዱ አሁን በመካሄድ ያለው የሙስሊሙ እንቅስቃሴ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በትላንትናው ዕለት ማለትም ተቃውሞው መሰረዙ እስከተገለጸበት ሰአት ድረስ በደም ብዛት፤ በልብ ድካም ና በአዕምሮ ጭንቀት አልጋ የያዘውን የወያኔ ብዛት ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ሙስሊሙ ታሪክ ሰሪ መሆኑን ያስመሰከረበት፡ እንደቀደምት ግዚያት የበይ ተመልካች ሳይሆን የሃገሪቱን የወደፊት ዕጣ ለመወሰን ዋነኛ ሃይል መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነበር በዚህም የኢትዮጵያ ሙስሊም 1- ወያኔ 0 ሆኖ ተሸንፉአል፡ እኔም የዚህ ተራሮችን ሳይሆን የኢትዮጵያን ምድር ከዳር እስከ ዳር ያንቀጠቀጠ ትውልድ አካል በመሆኔ ኮርቻለሁ፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment