Tuesday, October 8, 2013

ትዋል ትደር እንጂ አህያ የጅብ ናት

ትዋል ትደር እንጂ አህያ የጅብ ናት
አበው ሲተርቱ የፈለገውን ያህል ጊዜ ቢቆይ ሊቀር የማይችለውን ነገር እንደማይሆን አድርገው ለሚያስቡ ሰዎች በምሳሌ ሲያስረዱትዋል ትደር እንጂ አህያ የጅብ ናትይላሉ፡፡ እውነት ነው አህያ በህይወት እያለች ብትበላም የሚበላት ጅብ ነው፡፡ ረጂም ጊዜ ቆይታ ብትሞትም የሚበላት ጅብ ነው፡፡ ምክንያቱ ቤት ውስጥ ብትሞትም ጌታዋ አውጥቶ ለጅብ ይጥላታል፡፡ ጌታዋ ከጅብ ይጠብቃት ይንከባከባት የነበረው በህይወት እስካለች እስካገለገቺው ድረስ ብቻ ነው፡፡ ወያኔ አስተዳደር ህዝብ 22 ዓመት አንብቷል፡፡ ህዝብ እንደ አንድ አገር ህዝብ ሳይሆን እንደባዕድ እንደጠላት እንዲባላ ተደርጓል፡፡ ዜጐች በነፃ ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው እንዳይሰሩ ተደንግጓል፡፡ በይፋ አንተ አማራ ነህ፤ ኦሮሞ ነህ፤ አኟክ ነህ እዚህ መሥራት አትችልም እየተባለ ከሥራ ተባሯል፡፡ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል፡፡ አገር ተቆርሷል፡፡ አገሪቱ ወደቧን አታለች፡፡ ጥቂት ሎሌዎች ከብረዋል፡፡ አገሩ ላይ መብትና ክብሩ ተጠብቆለት የመኖር መብት የለውም።ጌታቸውን ከበው ይደሰኩራሉ፡፡ ህዝብ ግን ተርቦ፣ ታርዞ፣ ተዋርዶ ያያቸዋል፡፡ በአረብ ሃገራት ለባርነት ስራ በወያኔ እየተሸ እጣቸ ተገዶ መደፈር፣ በፈላው ወሃ መቀቀል፣ መደብደብ፣ በየባህሩ ላይ ሰምጦ መቅረት ሃገር እንደሌለው በየሰዉ ሃገር ላይ መዋረድና ከፎቅ ላይ እየተወረሩ ክቡር ህይወትን  ውድ እህቶች ሆኗል የሕዝብ ድምጽ ይከበርው በማለታቸ ስንቶች በየእስር ቤቱ ያለፍርድ ተወርውረው ቀርተዋል ፡፡ወያኔ ያሳጣንን ሰላምና ነጻነት፡ የቀማንን ሃገርና አንድነት እውነት ህዝብ ማሸነፉ የማይቀር ነው፡፡ ትዋል ትደር እንጂ አህያ የጅብ ናት፡፡ እንድንል ተገደናል፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ

   

ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

No comments: