ግንቦት7 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወገኑ ነጻነት የሚቆምበትን መንገድ እያዘጋጀ መሀኑን ገለጸ
ንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወያኔ የዘረኝነት አለንጋ የሚለበለበዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እራሱንና ወገኑን ነጻ የሚያደርግበትን መንገድ መከላከያ ሰራዊቱ ዉስጥ እየቀየሰ መሆኑን የንቅናቄዉ ዋና ጸሀፉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ። ዋና ጸሀፊዉ ይህንን የተናገሩት ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ዉስጥ የግንቦት ሰባት ኃይሎችን ለመርዳት በተደረገዉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ባሰሙት ንግግር ነዉ። አቶ አንዳርጋቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን አስመለሰክተዉ ባደረጉት ንግግር እንደዚህ አይነቱ ወገናዊ ዝግጅት በአንድ በኩል በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አባላት ዉስጥ ከፍተኛ መነቃቃት የሚፈጥር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ወራዊቱ የተጣለበት ህዝባዊ አደራ ምን ያክል ከፍተኛ መሆኑን የሚያስታውሰን ነው ብለዋል።
በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር ሀይል ከድተው ህዝባዊ ሰራዊቱን ስለተቀላቀሉት ጀግኖች ተጠይቀዉ በሰጡት መልስ የአየር ኃይል አባላቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዉ ንቅናቄያቸዉ በመከላከያ ሰራዊት፤ በደህንነት መስሪያ ቤትና በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ዉስጥ ወያኔ ሊደርስበት በማይችልበት መልኩ የግንኙነት መስመር እየዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል።
ኖርዌይ ኦስሎ ዉስጥ የተካሄደዉን አይነት የግንቦት ሰባት ኃይሎች የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሌሎች አገሮችና ከተሞች ዉስጥ ለማድረግ እቅድ አላችሁ ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ ህዝባዊ ሀይሉ ከተግባር ጋር በተዛመደ መልኩ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት መርሀ ግብሩን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በህዝባዊ ሀይሉ ወይም በግለሰቦች ስም ምንም አይነት የገቢ መሰባሰቢያ ዝግጅት እንደማይደርግ ገልጸዋል። በሌላ ዜና ደግሞ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኖርዌ፤ ሲዉድንና በአካባቢዉ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር እንደተወያዩ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ዉይይታቸዉ ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን ዓላማዎች፤ ተልዕኮዎችና ራዕይ በማስተዋወቅ ህዝባዊ ሃይሉ ከምስረታው ጀምሮ አሁን ድረስ ያለበትን ደረጃ በምስልና በጽሁፍ በተደገፈ ገለጻ ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።
ከአቶ አንዳርጋቸው እስካሁን ድረስ የተካሄደዉ የህዝባዊ ኃይሉ ስልጠና የንቅናቁዉን የአመራር አካላት ያካተተ መሆኑን ጠቅሰዉ ወታደራዊ ስልጠናዉ የበታችና የበላይ የሚባል ልዩነት እንደሌለበት አስገንዝበዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተዉ ቤተሰባቸውን፤ ስራቸውን፤ገንዘባቸውንና የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ከኢትዮጵያና ከመላው ዓለም በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እንደሆነ እንደሆነ ገልጸዋል። የግንቦት ሰባት ዓላማ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማስፈን ብቻ ሳይሆን ባለፉት 22 ዓመታት ኢትዮጵያውያን የተገፈፉትን ክብራቸውን ማስመለስ ጭምር መሆኑን አቶ አንዳርጋቸው አስምረውበታል።
No comments:
Post a Comment