ስርዓተ አልባኝነት (anarchism) የህወሃት አዲሱ
የሽብር ስልት!!
ህወሃት መራሹ ቡድን ባለፉት ሳምንታት በሰማያዊ ፓርቲና አንድንት ፓርቲ በተጠሩት ሰልፎች ላይ በተለይ አንድነት ሰልፍና
ህዝባዊ ስብሰባ ባካሄደባቸው ከተሞች ሁሉ የተከተለው አንድ ወጥ አሰራር ነበር፤
1. የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎችንም ሆነ ተሳታፊዎችን ታርጋ የለለው መኪና በሚያሽከረክሩ፤ ማንነታቸውን የሚገልጽ መለዮ
ባይለብሱ፤ መታወቂያ ማሳየት ውርደት መስሎ በሚታያቸው፤ መሳሪያ በመያዛቸው ብቻ ሌላውን ህዝብ ማፈን፤ ማሰርና
ማንገላታት
2. አዲስ አበባም በተደረጉት ስልፎች ላይ ማንነታቸው በማይታውቅ ግልሰቦች፤ መታወቂያቸውን ለፖሊስ እንኳ ማሳየት
በማይፈልጉ ቡድኖች ህዝብን ማንገላታት፤ ማፈን፤ ማሰርና የደረሱበት እንዳይታወቅ ማድረግ
እንዚህ መታወቂያም፤ መለዮም፤ የሌላቸው፤ ማንነታቸውን ለህዝብም ይሁን ለፖሊስ መግለጽ የማይፈልጉ ግን መሳሪያ ስላነገቡ
ብቻ ህዝብን እንደፈለጉ የሚያንገላቱ እነማነ ናቸው? ማ ላካቸው? አባይ ወልዱ? ስብሃት ነጋ? በረከት? ሃይለማርያም?
ወይስ ሌላ አካል?
ይህን መመለስ ባይቻልም በግልጽ የሚታየው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የጅምላ መንግስት ነኝ የሚለው አካል የማይቆጣጠረው
ወይም የማይቆጣጠራቸውና ከመንግስት ነኝ ተብየው አውቅና ወጭ የሚንቀሳቀሱ የወንጀለኞች ቡድን መኖሩ ነው፡ እነዚህን
ቡድኖች መንግስት የሚቆጣጠራቸው ከሆነ ደግሞ ነገሩን የበለጠ ያወሳስበዋል።
በዚህም ዞረ በዛ፤ ትልቁ ልብ ሊባል የሚገባው ቁምነገር፤ ህወሃት መራሹ ቡድን ህዝብን ከማሰቃየት፤ ከማሰር፤ ከመግደልና
ከማንገላታት ያለፈ የህዝብን ሰላም ለማስከበርና ደህንነቱን ለመጠበቅ ፈቃደኝነቱም ሆነ ብቃቱ የለለው መሆኑ ነው፡ ህወሃት
መራሹ ቡድን በመላ አገሪቷ ስርዓተ አልበኝነትን (anarchism) ማስፈንንና ህዝብን በሽብር አሸማቆ ማኖርን እንደ አማራጭ
የወሰደው ይመስላል፡
በየትም ሃገር ህግ አስከባሪ ነኝ የሚል ግለሰብ መታወቂያ ማሳየት የግድ ነው፤ ይህ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰራበት አደለም።
መንግስት ተብየው ያላከበረውን ህግ ህዝብ ያከብረዋል ተብሎ አይጠበቅም ስለዚህ የህወሃት ፍላጎት ስርዓተ አለበኝነትን
ማስፈን ስለሆነ ገፍቶበታል።
የያንዳንዱ ዜጋ ሰላምና ደህንነት በመንግስት ላይ ሳይሆን በራሱ በግልሰቡ እጅ ላይ ወድቋል፡ ህግና ስርዓት አክባሪው
የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ ወደ ስርዓተ አልበኝነት ማጥ ከወደቀ መመለሻው በጣም ከባድ ጦሱም ሊጠገን የማይችል ትልቅ አደጋ
ነው።
ለህወሃትም ሆነ ለአጃቢዎቹ አይበጃቸውም!!
ያሰፈራኛል!!
ድል ለተገፉ!

No comments:
Post a Comment