Saturday, October 12, 2013

ኢህአዴግ መናገር እንጂ መስማት አይፈልግም፡፡

ኢህአዴግ መናገር እንጂ መስማት አይፈልግም፡፡ ሐቅ ነው፡፡ መስማት የማይፈልግ ደግሞ ባለቅኔው እንዳሉት… ነው፡፡ ለነገሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ምንጫቸው እንጂ ሊለያይ የሚችለው መንገዳቸውና የአመራር መንፈሳቸው ከቃላት ለውጥ /ወታደራዊ፣ ህዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ/ በቀር አንድ ነው፡፡ የሐሳብ ልዩነት እንደ ጠላት ያስተያያል፣ ተሳስታችኋል የሚላቸውን ማጥፋት፣ ከእኛ ካልሆንክ ከጠላቶቻችን ነህ የሚል ታርጋ መለጠፍ፣ ሃሳባቸውን ያልተቀበለ ሁሉ የብፅዕና ጉድለት ያለበት አስመስሎ ማቅረብ ወዘተ ወዘተ የዝች አገር ፖለቲካዊ ታሪክ ነው፡፡ መቼስ ይችን አገር ከፍ ሲል እጥረት ዝቅ ሲል ደግሞ እጦት የሚባሉ ጐረቤት አገሮች ያዋስኗታል በፖለቲካውም በኢኮኖሚውም፡፡ ወይ በመንግስት አልተመን ወይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ተስፋ ማድረግ አልቻልን እንዴ ያለ እንቆቅልሽ ነው ባካችሁ? ህዝብ የሰጣቸውን ተልእኮ ወደ ጎን አድርገው የህዝብን ትግል ሜዳ ላይ በትነው እርስ በርሳቸው የሚናከሱ ተቃዋሚዎች ባሉበት አገር ለህዝቡ ፍላጐት ተገዢ የሆኑ ተቃዋሚዎች የአልማዝ ያህል ውድ በሆኑባት አገር አንዳች ፖለቲካዊ ለውጥ በአጭር ጊዜ ይመጣል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ ይሁን እና ‹‹ዝምታ ለበግም አልበጃት›› እንዲሉ ዝም ብሎ ማየቱ ተገቢነት የለውም፡፡
አዎ! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

No comments: