ከኔ በላይ ለአገሪቱ ተቆርቆሪ
ወገን የለም ብሎ የሚያስብ ገዢ ፓርቲ እና ይህን ሀሳብ የመጨረሻ እውነት አድርጐ የሚቆጥር የካድሬ ጐርፍ፣ የማያባራ የምሁራን እና
የዜጐች ስደት (ያውም በሬድዮ ጭምር በሚለፍፉ የውጭ አገር የሥራ ዕድል ማስታወቂያ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ እስክንደርስ፡፡)፣ በዘፈቀደ
የተቀመጠ ግትር ፖሊሲ መቃብራቸውን መማስ፣ የታዋቂ ፖለቲከኞች እና የጋዜጠኞች እስር እና ወከባ እንዲሁም ተመሳሳይ ሕዝባዊ በደሎች፤
በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እጦት እና የሙስና መንሰራፋት የተባባሱት እና የተበራከቱት በሌላ በማንም አይደለም፡፡ ማነው ተው
የሚለኝ? ሊጠይቀኝ የሚችል ከኔ ጋር የተጠጋጋ ኃይል ያለው አካል ከወዴት አለ? እኔን የሚመጥን ጉልበተኛ ማን አለ? ከኔ በላይ
አዋቂ፣ ከኔ በላይ ብልህ፣ ከኔ በላይ አስተዳዳሪ ለዘበት በሚል መንግስት እንጂ፡፡
በኑሮ ውድነት፣ በአንድ
ፓርቲ የበላይነት በዴሞክራሲ እና በብልሹ አስተዳደር እንዲሁም ቀጣይነት በሌላቸው እና ፖለቲካዊ ዓላማቸውን እስካልሳቱ
ብቻ በሚጸድቁ ፖሊሲዎች የተሰላቸው ህዝብ፣ አነሰም በዛም የሚያውቃቸውን እና የሚያከብራቸውን ከመንግስት በተቃራኒው የቆሙትን ፓለቲከኞች
እና ጋዜጠኞች በሽብርተኝት ታርጋ ከለላ ወደ እስር ቤት መወርወር፤ ግለሰቦቹን እና ደጋፊዎቻቸውን ብሎም የሰላማዊ ትግልን ወዳድ
ህብረተሰብ ብቻ የሚጐዳ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ሊመስል ይችላል፡፡ ይህ የሚመስለው ግን ከላይ ከላይ ብቻ የታየ እና የታሰበ እንደሆነ
ነው፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከአባላቶቻቸው እና አመራሮቻቸው ከመታሰራቸው እና ሌሎች አቅምን ከሚፈታተኑ ሁኔታዎች
ጋር ተያይዞ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፉ እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ እውነታ ነው፡፡ እንደውም አሁን ያለው አዝማሚያ ሰላማዊ ትግሉን እና
የዴሞክራሲያዊ ሽግግሩን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ ከቶታል፡፡
በነዚህ በሁለት አካላት
መሐል ደግሞ ሕዝቡ አለ፡፡ አሁንም ከድህነት፣ ከርሀብ እና ከስደት አዙሪት መውጣት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳልቻለ የሚነግሩንን ብዙ
ምሳሌዎች መጥቀስ የሚያቅተው ሰው እንደሌለ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የሰሞኑ የመንግስት አቋም እና በኮሚኒስታዊ ስልት የተቃኙ እርምጃዎች
(የእስር እና የመፈክሩን ጋጋታ ልብ ይሏል)፤ የኮሚኒስት ሥርዓት አራማጆችን ውድቀት እና ድቀት በራስ ላይ ከመጋበዝ እና በራስ
ላይ ከማሟረት በተለየ መልኩ እንዳለየው መገመት ይቻላል፡፡
ወያኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር
እየሰደደ በመጣው ኃይሉ እና ባለው የፖለቲካ ሥልጣን ልዕልና በመጠቀም፤ በእያንዳንዱ እርምጃ እና ድርጊት ያለመጠየቅን ፀጋ ተጐናጽፏል፡፡
ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ማየት፣ የፈለጉትን ሕግ በፓርላማ ማፅደቅ እና በዚህ ሕግ ሌሎችን ማሸማቀቅ እንዲሁም ማስጨነቅ፣ የሌሎችን ሀሳብ
እንደ መናኛ ቆጥሮ የራስን ሀሳብ ብቻ መናገር እና ማስነገር (የሀገሪቱን ትላልቅ እና ኃይል ያላቸው የመገናኛ ብዙሀንን ለራስ ብቻ
በማዋል የሌሎችን ሀሳብ በመገደብ፡፡)፣ ሌሎችን ባለድርሻ አካላት ሳያማክሩ አገሪቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ሥነ
ምጣኔያዊ ውሳኔዎችን ማስተላለፍ፤ ተው የሚለኝ ካለ፤ ይሞክረኝ! የሚል ሀላፊነት የጐደለው መልዕክት ማስተላለፍ እንጂ ሌላ ምን ሊሆን
ይችላል? ስለዚህ ወያኔንን ለማሸነፍ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት መነሳትና መተባበር ይሻላል እላለሁ፡፡
ከአንድነት ብሎግ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
No comments:
Post a Comment