Tuesday, October 29, 2013

500 መቶ ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት የባለስልጣኑ ኦዲተሮች ጥፋተኛ ተባሉ

500 መቶ ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት የባለስልጣኑ ኦዲተሮች ጥፋተኛ ተባሉ 

500 መቶ ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሁለት የባለስልጣኑ ኦዲተሮች ጥፋተኛ ተባሉ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 15፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት 500 መቶ ሺ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በተያዙ ሁለት የገበዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኦዲተሮች ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ።
ተከሳሾች አይሸሽም ገብሬ እና አክሊለብርሀን አባቡ ከባለስልጣኑ ዲኦትራኮን ወይም ጄነራል ኢትዮጵያ ኦቨርሲስ ትሬዲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቆዳና ሌጦ ግብዓት አቅራቢ ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ኦዲት አድርጉ የሚል ትእዛዝ ይሰጣቸዋል።
በታዘዙት መሰረት ኦዲት አድርገው ሳያጠናቅቁ የድርጅቱን ስራ አስኪያጅ አቶ ኢብራሂም አስፋውን በሰራነው ኦዲት መሰረት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ዕዳ ስለተገኘብህ 1 ሚሊዮን ብር ጉቦ ስጠን ይሏቸዋል።
ስራ አስኪያጁ በድርድር ጉቦውን ወደ ግማሽ ሚሊዮን ዝቅ በማድረግ ሰኔ 26 2004 ምሽት 12 ሰዓት ገደማ ሳሪስ አቦ ቀለበት መንገድ አካበበቢ ብሩን ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
ችሎቱ ከከሳሽ የኮሚሽኑ አቃቤ ህግና ከተከሳሽ የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ውሳኔ ለመስጠት ፥ ለጥቅምት 22 2006 ቀጠሮ ይዟል።

No comments: