የኤርትራ ስደተኞች በኢትዮጵያ፤ ብሦትና ግጭት
በምዕራብ ትግሪይ በአዲ ሃርሽ እና አዲ ዐይኒ መጠለያ ሠፈሮች ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ይደርስብናል የሚሏቸውን በደሎች ያሰሙበትን፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የጠየቁበትን ሰልፍ በቅርቡ አድርገዋል፡፡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወት ጠፍቷል፤ ሰው ተጎድቷል፡፡
15.10.2013
አዲስ አበባ፣ አዲ ዐይኒ፣ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
በምዕራብ ትግሪይ በአዲ ሃርሽ እና አዲ ዐይኒ መጠለያ ሠፈሮች ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ይደርስብናል የሚሏቸውን በደሎች ያሰሙበትን፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩ የጠየቁበትን ሰልፍ በቅርቡ አድርገዋል፡፡
ምንም እንኳ ሰልፉ ቀድሞም በውስጣቸው የነበሩ ብሶቶችን ያወጡበት ይሁን እንጂ ሜዲቴራኒያን ባሕር ውስጥ በጣልያኒቱ ላምፔዱሳ ደሴት አቅራቢያ የተፈጠረው ዓለምን እንደገና ያስደነገጠ የጀልባ መስጠም አጋጣሚ ነው የታሪኩ መነሻ፡፡
አዲ ዐይኒ የሚገኙት የኤርትራ ስደተኞች ብዙ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች አሏቸው፤ ለብዙ ዓመታት በሠፊሮቹ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች እያሉ በእነርሱ ስም ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌሎች ተቀባይ ሃገሮች እንዲሄዱ እንደሚደረግ፣ መብቶቻቸው እንደሚሸጡና ሙስና እንደበረታ አመልክተዋል፡፡ አፋኞችና ሕገወጥ ሰው አስተላላፊዎች በሰፈሮቻቸው ውስጥ ችግር እንደሚፈጥሩባቸው ተናግረዋል፡፡ የሴቶችና የሕፃናት መብቶች እንዲከበሩ ጠይቀዋል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የላምፔዱሣ አደጋ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻቸውን በሻማ ለመዘከር ከወጡ በኋላ ሌሎች ጥያቄዎቻቸውን ለማሰማት ሲሰለፉ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሕይወት ጠፍቷል፤ ሰው ተጎድቷል፡፡
አሠራሩ ለሙስና የሚመች እንዳልሆነ የሚናገረው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጉዳዩን በቅርብ እያጠና መሆኑን ገልጿል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

No comments:
Post a Comment