በኖርዌይ ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ በስኬት ተከናወነ::
ሴፕቴምበር 28,2013 በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልን ለመርዳት በኖርዌ ኦስሎከተማ የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የህዝባዊ ሃይሉ ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ እና የግንቦት 7የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንንና ጥሪ የተደረገላቸ እንግዶችና ከተለያየ የአውሮፓናስካንዴኔቪያን ሃገሮች መጡና በጣም በርካታ የሆኑ በኖርዌ በሚኖሩ ከተለያየ ከተማ የመጡ ሀገር ወዳድኢትዮጵያውያን በተገኙበት በታላቅ ወኔና የሃገር ፍቅር ስሜት በስኬት ተከናወኖ አመሸ።
በዝግጅቱ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይሉ አመራር ስለድርጅታቸው በሰፊው ህዝቡን ያስደሰተ ማብራሪያ የሰጡሲሆን ከታዳሚው የቀረባላቸውንም ጥያቄዎች በስፋት በማብራራት ለታዳሚው ከፍተኛ ግንዛቤአስጨብጠዋል። በተመሳሳይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በምስል የተደገፈ ከፍተኛ ማብራሪያ ሰጥተው ከህዝብየቀረበላቸውን ጥያቄዎች ሰፋ አድርገው አስረድተዋል።
በአንፃሩ እጃችን እረጅም ነው ብለው የሚያስቡ ጠባብ አስተሳሰብ ያላቸው የወያኔ ተላላኪ ቡድኖች ዲሞክራሲባለበት በኖርዌ ምድር መጥተ እንኳን የማይቀየሩ አምባገነኖች እዚህም ዝግጅታችን እንዳይሳካ ለማበላሸትእንቅልፍ ሳይተኙ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን እየነፉ ህዝብ ለማደናገር የአሸባሪ ድርጅት ለመርዳት የገቢማሰባሰቢያ ሊያደርጉ ነበር ነገር ግን ፕሮግራሙ ተሰረዘ በማለት ዜና ቢያሰራጩም እኛ ግን እየረዳን ያለነውየግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል በየትኛውም አለም በአሸባሪነት መዝገብ ውስጥ ያልተመዘገበ ድርጅት መሆኑን የኖርዌፕሮፌሰር በሃገሪቱ ውስጥ ለሚታተም አንድ ጋዜጣ አስተያየታቸውን የገለፁ ሲሆን በእለቱም ዝገጅቱ በደማቅሁኔታ ተከናውኖ ከዚህ ቀደም በየተኛውም የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮገራም ያልታየ ከፍተኛ የገንዘብ ገቢምተደርጓል።
በአጠቃላይ በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ጨረታዎች፤ ቀስቃሽ ሙዚቃ፤ ባህላዊ ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩቁሳቁሶች ለሽያጭ ቀርበው የነበረ ሲሆን በተጨማሪም የትጥቅ ትግል ለምን አስፈለገ በሚል አጭር ገላጭ ድራማቀርቦ ህዝቡን በጣም አስደስቷል። በዝግጅቱ መክፈቻና መዝጊያ ላይም የህዝባዊ ሃይሉ መዝሙር ላንቺ ነው ሃገሬላንቺ ነው የሚለው በህዝቡ ተዘምሮ ዝገጅቱም እኩለ ለሊት በድምቅት ተጠናቋል፡፡
http://ethsat.com/video/esat-fundraising-event-for-g7-popular-force-in-oslo-oct-6-2013-ethiopia/
http://ethsat.com/video/esat-fundraising-event-for-g7-popular-force-in-oslo-oct-6-2013-ethiopia/
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ሞት ለወያኔ
No comments:
Post a Comment